🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ከመጽሐፍ ገጽ ዝጎራ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ከመጽሐፍ ገጽ
ዝጎራ
አለማየሁ ዋሴ እሸቴ

“እውነት አለህ የእኔ ልጅ ! ይሁንና ሞት ብትፈራውም ብትንቀውም የማይቀር ዕዳ ወይም መንገድ ነው፡፡ የዕድሜህ ማጠር ወይም መርዘም አያስጨንቅህ፤ የፈጣሪ ፈቃድ ነውና፡፡ ይልቁንም በተሰጠችህ እያንዳንዷ ቀን በመልካምና በደስታ ለመኖር ሥጋህን ተጠንቀቀው፤ ነፍስህን ቁጠራት፣ እምነትህን ጠንቅቀው”
“ኢትዮጵያዊነት በአምስት አምዶች የታነጸ መኖሪያ እልፍኝ ነው፡፡ ጥልቅና ሰፊ ዕውቀት፣ መዛል የሌለበት ትጋት፣ በትዕግስት የታሸ ጀግንነት፣ ርኩሰት የሌለበት ቅድስና፣ ግብዝነት የሌለበት ምስጢራዊ ሕይወት ነው!”

“የምሥጢር ሙዳይ ሁን እንጂ የእሳት ማንደጃ ወናፍ አትሁን፡፡ ሰዎች ሊሰሙህ በሚችሉበት ችሎታቸውና ፍላጎታቸው መጠን ብቻ ተናገር፣ ቁጥብ እንጂ ዝርው አትሁን፡፡ ለእውቀት ትጋ፡፡ በከፊል በተረዳ¤ው ነገር ራስህን እንደአዋቂ አትቁጠር፡፡ በከፊል ከማወቅ አለማወቅ ይሻላል፡፡ ሥራ ስትሰራ ደግሞ ነገ ትቼው ለምሞተው ወይም ብሠራ የሚጠቀመው ሌላ ነው በሚል ተስፋ ቢስ ሆነህ ሳይሆን ዘላለም እንደምትኖር ያክል በመትጋት ነው፡፡ ትጋት ጥሩ ነው፡፡ ችኮላህ ግን ውጤት አያመጣም ፤ በችኮላ መሥራት እና በፍጥነት መሥራት የተለያዩ ናቸው፡፡ ርኩሰት የዕውቀትና የሥልጣኔ መገለጫ አይደለምና ማንነትንና ሰብዓዊ ክብርን ከሚያጎድፉ ተግባራት መታቀብን ገንዘብ አድርግ፡፡”

“እናም በየዕለቱ በኑሮህ ጠንቃቃ ሁን፡፡ ያለጸጸት ነገን ለመኖር ዛሬን በቁም ነገር አሳልፍ፤ ውሳኔዎችህ ትክክለኛ መሆናቸውን መርምር፤ ልክ እንደገና ሕይወትን የመኖር ዕድል ቢኖርህ ወይም እንደገና የመወለድ ዕድል ቢኖርህ ደግመህ የምትኖረውንና ለማከናወን የምትመርጠውን ዐይነት ሕይወት ለመኖር ሞክር ፡፡ እንዲህ ያለ ጥየቄ ብትጠየቅ መልስህ ምንድን ይሆን? አንደገና የመወለድ ምርጫ ቢኖርህ ኢትዮጵያ ውስጥ ኢትዮጵያዊ ሆነህ ለመወለድ ትመርጣለህ? የያዝከውን ሙያ በድጋሚ ትመርጠዋለህን? ያገባሃትን ሚስትህን እነደገና ታገባታለህ ወይስ መነኩሴ ከሆንክ እንደገና ምንኩስና ሕይወትን ትደግመዋለህን? ……….….”

“…የምትፎካከሩባትን፣ ሲያሻችሁ የምትወዷትንና የምታወድሷትን ስትፈልጉ ደግሞ የምታዋርዷትን፣ በለስ ሲቀናችሁ ከላይ ሆናችሁ ስትረግጡ ሌላ ጊዜ በተራችሁ ከሥር ሆናችሁ ስትታሹ የምትኖሩባትን ሀገራችንን፣ የትጋትና የበረከት ምድር መሆኗ ይገለጽ ዘንድ፣ ለራሳች ላይ ያራቅነውን ጸጋ እንጎናጸፍ ዘንድ ፣ፈጣሪ ለተስፋው የሰነፈውን ልባችንን ያነሣሣው ዘንድ፣ የመከራችን ፍጻሜ ይቀርብ ዘንድ የሰጠንን እናስተውልበት ዘንድ ኅሊናችንን በብርሃኑ እንዲሞላው በዚህ ቦታ እንለምነዋለን፡፡ የተናቀውንና የተረሳውን ጥበባችንን የሚፈልገው ትውልድ እስኪመጣ ድረስ በእምነት አደራችንን በአርምሞ የምንጠብቅበት ስፍራ ነውና ከዚህ በላይ አትድፈረው……”

“የኔ ልጅ ይልቁንም፡ -
‹‹ፈጣሪ ለምን አይሰማንም ሳይሆን ለምን አንሰማውም፣ ፈጣሪ ለምን አይባርከንመ ሳይሆን ለምን በረከታችንን አናውቅም ማለትን ተማሩ፤ ለምን ተወን አይደለም ለምን ተውነው በሉ፤ ለምን የብልጽግና ቁልፍ ደበቀብን ሳሆን ለምን ችሎታችንን ስንፍና ጉድጓድ ውስጥ ቀበርን፣ አቅማችንን ለምን በልግመት ስልቻ ከተትነው›› በሉ!”
“ ሌላወን መስላችሁ ሳይሆን ራሳችሁን ሆናችሁ ለማደግ ሞክሩ……….”

‹‹ዝጎራ››


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19