ነፍስ ይማር ስለኔ ስላንቺ ካህናት በወረብ ፣ ሼሆች በመንዙማ ባርምሞም በጩኸት፤ ይቀኛሉ ቅኔ ፣ ይዜማሉ ዜማ ቅዱስ ለፍቅራችን ቅዱስ ለጠባችን ቅዱስ ለፍጻሜው በንባሽ ታንቆ ፍቅር ፣ ላለቀበት እድሜው ስብሃት ሶስቴ ላንቺ ፣ ስብሃት ደግሞ ለኔ ለደከመው አካል ፣ ለደቀቀው ጎኔ ፍትሃት ለዛ ፍቅር ፣ ፍትሃት ለዛ ተስፋ በኩርፊያሽ ተዳፍኖ ፣ በእምባሽ ለጠፋ ወዩ ለትግስትሽ ፣ ሞቷል መጠበቄ ነፍስ ይማር ለሳቅሽ ፣ ነፍስ ይማር ለሳቄ [ቶማስ ትግስቱ] 1.5K viewsAbela, 14:53