Get Mystery Box with random crypto!

ጊዜ ሎተሪ ነው ጊዜ ባለእድል ባለ እጣ ከዘረሰብ ደጃፍ ገብቶ የሚወጣ ጊዜ ክፉ ፊደል ጊዜ ክፉ መ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ጊዜ

ሎተሪ ነው ጊዜ ባለእድል ባለ እጣ
ከዘረሰብ ደጃፍ ገብቶ የሚወጣ
ጊዜ ክፉ ፊደል ጊዜ ክፉ መምህር
ብራና ዘርግቶ ሁሉን የሚያስተምር
ሻረ ሲሉት መግል ወይ ሲመግል ሽረት
በነተበ አለላ አዲስ እንደመስራት።
የጊዜ ማሲንቆ ሲቃ እየተቃኘ
ሰውነት ረክሶ ባፈር እየናኘ
እንደ ተራ ነገር እንደሆነ ኦና
ስንት የበላ ጎጆ በስንቱ የፀና
ምንም እንዳልሆነ እግር ይሄዳል ትቶ
ኋላን እየረሳ ፊቱን ተመልክቶ
ዳሩ ምን ያደርጋል
ልብ መች ይርቃል
በደከሙ አይኖቹ እንባ ይወርባል
በቅዥት አለሙ ህልም ያመረግዳል።
ጊዜ ክፉ ሎሌ ጊዜ ክፉ ጌታ
የመነኩሴ ግዝት የወልይ እሪታ
የጀንበር አርምሞ የጨረቃ ዋይታ
ጊዜ ሴት ወይዘሮ ጊዜ ጋለሞታ።
ወዲህ ግልብ ቅኔ ወዲያ ባለ ምስጢር
ካልዋሉበት ማሳ እህል እሚሰፍር!!


11/02/2014
ሳሮናዊት እንድሪስ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19