🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ድንቁርና ሲጮህ አዋቂነት ዝም ይላል* አህያ ለነብር ሳር ሰማያዊ ቀለም እንዳለው ይነግረዋል ። ነ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ድንቁርና ሲጮህ አዋቂነት ዝም ይላል*

አህያ ለነብር ሳር ሰማያዊ ቀለም እንዳለው ይነግረዋል ። ነብርም አይ አይደለም
አረንጓዴ ነው ይላል። እንዲህ እንዲህ እያለ በመሃከላቸው ያለው ክርክር እየሞቀ
ሄዶ መግባባት አቃታቸውና እንዲ ሸመግላቸው የጫካው ንጉስ ወደሆነው ወደ
አንበሳ ይሄዳሉ። ከዚያም አንበሳ ጋር እንደደረሱ አህያ እየጮኸች ክቡርነትዎ
'እውነት አይደል! ሳር ሰማያዊ ቀለም አይደል ያለው?' ትለዋለች። አንበሳም
በትክክል በማለት መለሰላት። አህያም አሁንም ወደ ፊት ጠጋ በማለት ነብር
በእኔ ሃሳብ አይስማማም፤ እኔን ይቃረነኛል ስለዚህ አስቆጥቶኛልና እባክህ
ይቀጣልኝ አለች።አንበሳም በጥሞና ከአዳመጠ በኋላ ለ5 አመት ነብር ምንም
እንዳያወራና ዝም እንዲል በማለት ፍርዱን አሳለፈ።አህያም በፍርዱ ተደስቶ
እየዘለለ 'ሳር ሰማያዊ ነው' በማለት አየጮኸ ሄደ።
ነብርም ፍርዱን ተቀብሎ ሲያበቃ ክቡርነትዎ ሳር አረንጓዴ ሆኖ ሳለ ለምን
ቀጣከኝ? አለ።
አንበሳም እንደዚህ መለሰ ፦'በእርግጥ ሳር አረንጓዴ ነው።' ነብርም ታዲያ ለምን
ቀጣሃኝ አለው?
አንበሳም መለሰ ' ሳር አረንጓዴ ወይም ሰማያዊ መሆኑ ጥያቄው ምንም
አያደርግም። እኔ ይህን የወሰንኩት እንደ አንተ አይነት ንቁ አስተዋይና ብልህ የሆነ
በማይረባ ነገር ከአህያ ጋር እየተከራከረ ጊዜውን እንዳያጠፋና ሌላ ጊዜ እንዲህ
አይነት ነገር ወደ እኔ እንዳይመጣብኝ ነው አለው።
በመቀጠልም እንዲህ አለው 'ብዙው ሰአት የሚጠፋው ከሞኝ ጋር በምታደርገው
ክርክር ነው።'ሞኝ ስለ እውነት ወይም እውነታነት ሳይሆን የሚጨነቀው ስለ
ድልና ስለ እምነቱ ነው። በመጨረሻም 'ድንቁርና ሲጮህ አዋቂነት ዝም
ይላል!'አለው።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19