🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ያንን ለሊት ልታነጊ ከድቅድቅ ስር ስታመሺ ጨዋነቱ መች ጎሎ ነው ዝም ያለሽ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ያንን ለሊት ልታነጊ ከድቅድቅ ስር
ስታመሺ
ጨዋነቱ መች ጎሎ ነው ዝም ያለሽን
ምትረብሺ
( አቤት አንቺስ )
ካፈጣጠር ብዙ እርቀሽ መመለስን
ስትሰውሪ
ክንፍም አለሽ አዎ አውቃለው በእርምጃ
ነው የምትበሪ

(አጀብ ለኔ)

ከጥላሽ ጋር ውል የገባው መገለጥሽ
ሚናፍቀኝ
ሁሉንሽም አወኩኝ ስል ፍፁምነት
ሚጨርሰኝ
አወይ ለኔ....
አንቺን ብዬ ዳር ለያዝኩኝ
መመለስሽን ፍለጋ መሄድሽን የቀጠርኩኝ
መጨረስ ነሽ ዝንተ አለሙን
የመንጠፍጠፍ መውረድ ደራሽ
ሊያሳይ ነው የከተብሽ ገነት አይደል
ያንቺ ስፍራሽ
የማለዳ የወፍ ዜማ ጉም የያዛት ነሽ
ወገግታ
የመሳካት ነሽ አንኳሩ የስለቴ ዋና ቦታ
ስፀልይ ነው የምጀግን ስረጭሽ ነው
ምበረታ
ፀበል ፈውስ ለድክመቴ የአምላክ ቃሉን
ማስታወሻ
የእኔ እምነት ትክክል ነው የክርክር
ማጣቀሻ
የመአበል የዝምታው የማለቆች
መንቀራፈፍ
ወጀብሽን ስታበዢ በኪዳንሽ የምንሳፈፍ
መውረድ ነፅቶ መበከልን እዛ ጥሎ
ከደግ ጋር እያወጉ ቅድ ስናን ተመስሎ
ደሞ ደርበብ መቀዛቀዝ
ከብዙ ጋር ምንም አለ በመድመቅ
ውስጥ ሚደበዝዝ
ከሰራሽኝ ሰው መሆን ላይ አፍቃሪነት
ሲሽኮረመም
የኔን ማለፍ ፈቅጄ ነው በጣሮች ውስጥ
አንቺን ማክም
****************
(ካሊድ አቅሉ)