🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

'ላንቺ . . . ብለሽኛል - ያን ነኝ! ላንቺ መታመን ነው - አምላክ የሚያደርገኝ። - ያልሽ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

"ላንቺ . . .

<<ዐድማስና ክንፌ - መብረሬ ማረፌ
የፍካሬዬ ዓለም - ትንቢት መጽሐፌ...>>
ብለሽኛል - ያን ነኝ!
ላንቺ መታመን ነው - አምላክ የሚያደርገኝ።
-
<<ደስታና ፍቅሬ - ተስፋ አየር መኖሬ
እውቀትና ሙቀት - ስንቀ ዘላለሜ
ሰማዬ ምድሬ - ዛፍ ጥላ ፍሬዬ...>>
ያልሽውንም - ያን ነኝ!
ላንቺ መሞቱ ነው - እኔን የሚያኖረኝ።
...
አስቀድሞስ ቢሆን የፍጥረት ዘር እጁ
ላንቺ መንገድ እንጅ -
መች እግር አድርጎኝ ሢሠራኝ በደጁ።

ላንቺ መንገድ ጥርጊያ
ላንቺ አስቀድሞ ቃል -
ትም'ርት ወንጌል መርጊያ!
ላንቺ ንድፍ ዮሐንስ -
ለሙሉ ስዕልሽ ለሚሆን ኢየሱስ!

ለመጬመር ያህል...
አሽዋው የአብርሐም
የያዕቆብ ኮከብ ዘር
ቃል እየቸገነ
ግዛት እስኪጠበው - ኃይል እያገነነ
የበዛው --- የፈላ --- የረባው
ፈጣሪ ከፍጡር ካንቺ እስኪወለድ ነው።

ዲበኩሉ ጌታ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19