🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ዘመኔ ቀለም ፧ ፧ ፧ ገላን ማብከት ሆነኝ ተብሎ ልብስን መቅደድ የሚያስደንቅ ኖሩ ሚያስብል የዘመኑ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ዘመኔ ቀለም



ገላን ማብከት
ሆነኝ ተብሎ ልብስን መቅደድ
የሚያስደንቅ
ኖሩ ሚያስብል የዘመኑ ድንቅ መውደድ፡፡
ካ'ለም ጋርዶ
ከሟች አስበልጦ
በቋሚ አስጨፍልቆ ሰወንና ቀልቡን ማውረድ
እያዩ ማያዩት
ሰምተው ማይሰሙት
የሰው ጥላ መፍጠር የጊዜያችን ታላቅ ማበድ፡፡
ልብሱን መቅደድ
ድንቅ መውደድ፡፡
ቀልቡን ማውረድ
ታላቅ ማበድ፡፡
አይደል ማበድ
በውሃ የሚያልቅ ጨርቅን መቅደድ፡፡
አይደል መውረድ
ኗሪን መምራት በሟች መንገድ፡፡
ሰምተን ባንሰማ'ንጂ
መለኮት ነግሮናል
ፍቅር እንደሚያወርድ ከሰማይ ዙፋኑ፡፡
ልብ ባንል'ንጂ
በፍቅር ያበዱ
ለጽድቅ የተጠሩ በሰው አቅም ያመኑ
ስናየው ኖረናል
ጨርቅ ማቄን ሳይሉ
በዕድሜ ልካችን ልክ ካ'ለም ሲመንኑ፡፡
ሰማይ ቄስ አይነት ነው
ክብር አጎናጽፉኝ
ይላል አወድሱኝ ይወዳል ቡራኬ
አመሉን ስለማውቅ
በታጠፈ አንጀቴ
ዝናቡን ለመንኩት ቆሜ ተንበርክኬ፡፡
አረ እኔን ጨነቀኝ
ከሰማዩ ይብስ
ፍቅሬ ያወረደው ከፋብኝ አምላኬ፡፡
ሰማይ በቄስ አምሳል
አምላክ በኩሩ አካል
ሆነው ቆመው ፊቴ የዝንት ሆነ ብርኬ፡፡
< ሰማይ መቀመጫህ
ምድር መረገጫህ.....>
ብለው ያገነኑት ቄሱ የሰበኩት
ፈጣሪ ዘንግቷል
መሆኑ ጠፍቶታል
አካሌ ምድርነት ነፍሴ ሰማይነት፡፡
እኔን ተረግጦ
እኔ ላይ ተቀምጦ
ገድሉን ያገዝፋል በቄስ ገዛችነት፡፡
ግዝት እፈራለሁ፡፡
እንጰረጰራለሁ!!!
ያ'ምላክ አጋፋሪ ገበዝ እሸሻለሁ፡፡
ስሞት እንደሚኖር
ሳልኖር ዲዳ እንደሆን
ሁሉን እያወኩ ለቃሉ እሰግዳለሁ፡፡
ግዝት እየፈራሁ
ገበዝ እየሸሸሁ
አንዳንዴ ስጀግን
ከሰው አውድ ርቄ
አምላክ ተብዬውን እንዲ እጠይቃለሁ፡፡
ለምን!?
ለምን!?
ለምን!?
ለምን....
ለምን እንዲህ ሆነ
ብዬ እወጥራለሁ አስጨንቀዋለሁ!!!!
እሱም ተረጋግቶ
እንዲህ መለሰልኝ በሽንፈቴ ተነቃቅቶ
ቅፅበት ንቃቴ ሳይረብሸው
ቀጭን ፍርሃቴን አሳይቶ
ድንድን ድፍረቴን
በምጣድ ሳይሆን በክብ ዓለሜ አነጉቶ፡፡
ከአቻዬ ሳይሆን
ከቄሰ ገበዙ ከሰይጣኔ ከፍቶ፡፡
አለኝ....
" ምድር አረገዘ
ዘር እሸት ወለደ ሰማይ በወሰበ
ሊሰፋ የፈጠርኩት
መብል ያጠበበው የሰው ሆድ ጠገበ..."
አለና መለሶ
መለኮት ታላቁ አንገቱን ዘለሰ፡፡
የቄሱን አክብሮ
የምስኪን ታካቹን የኔን አንኳሰሰ፡፡
እኔም.....
< ካምላኩ ያወቀ...>
ፍጡር አልኩኝና መቅሰፍቱን ፈርቼ
መጻ'ፍ እንዳላጥብ
ለሰው ተራቅቄ በራሴ ከፍቼ
ይኸው እኖራለሁ
ለጥበብ ጠባቡን
ለምግብ ኅልቁውን ሆዴን ብቻ አስፍቼ፡፡
ፍቅር ጠራኝ ባለ
በኔ ላይ ተራምዶ
በኔው ላይ ተቀማጭ አምላክ ተጣልቼ
ሰማይ የሚመስልን
ክብር ያደለበውን
የገበዙን ዱላ ግዝቱን ፈርቼ፡፡
ሳላብደው አብጄ
ሳልወደው ወድጄ
ሞቴን ረስቼ
ሕይወት ነው እላለሁ
አዲስ ረስቼ ልማድን ለምጄ፡፡
እኔኑ አርሳለሁ
መውደድ ነው ያሉኝን መንፈዜን ጠምጄ፡፡
መሆኔን አርክሼ
ድንቅ ላሉት እብደት ጨርቄን ቀዳድጄ፡፡

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19