🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

መርዶ አታርዱኝ ሰዎቹ አምነዋል ቤታችን ስገባ ጉዝጓዝ ተጎዝጉዛል ፍራሾቹ ወርደው መሬት ተነጥፈዋ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

መርዶ አታርዱኝ

ሰዎቹ አምነዋል
ቤታችን ስገባ ጉዝጓዝ ተጎዝጉዛል
ፍራሾቹ ወርደው መሬት ተነጥፈዋል
ፍሪጁ ቲቪያችን አቡጀዲ ለብሷል
አንዷ ደሞ መጣች ነጠላ ዘቅዝቃ
የት ሄደ ደግ ሰው ጠየቀችኝ አንቃ
ምንም መልስ ሳልሰጣት
ዞሬ እነኳን ሳላያት
ፎቶህን እያየው አንድ ቃል ነገርኳት
የኔ ባል አልሞተም አታልቅሺ አልኳት
እዛ የነበረ ሁሉም ደነገጠ
እንባ እያወረደ ከንፈሩን መጠጠ
ምን ያደርግልኛል....
ከንፈር መመጠጡ
ምን ያደርግልኛል....
እንባቸው መፍሰሱ
አንተን አይመልሱ
ጎጆዬን አይቀልሱ
የእነሱ ዋይ ዋይታ
የእነሱ ዋይ ዋይታ
በአንድ ቀን ታይታ
ከሰልስት
ከአርባው
ደሞም ከ ሰማንያው
የማትዘልቅ ናት
ግና ግን
ግና ግን የኔ ባል
ስምህ ለዘላለም ሲወሳ ይኖራል
በከንቱ አለም ላይ ደግነትህ ገኗል

ሐና ይመር

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19