Get Mystery Box with random crypto!

[ የአንደበቴ መዝጊያ ] አልጋዬ ላይ ሁኜ ስለ አንች እያሰብኩ የፍቅሬን መግለጫ ቃላት እዬመረ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

[ የአንደበቴ መዝጊያ ]

አልጋዬ ላይ ሁኜ ስለ አንች እያሰብኩ
የፍቅሬን መግለጫ ቃላት እዬመረጥኩ
በፍቅር ውቅያኖስ ገብቼ እየዋኜሁ
ብዙ ተፈላሰፍኩ በዝምታ ሰመጥኩ
የፍቅሬን መግለጫ ቃላትን አመረትኩ
አሁን አንችን ማግኘት መንገር ብቻ ቀረኝ
ልነግርሽ ወስኜ ከአልጋዬ ወረድኩኝ
የምትወጭበትን ሰአቱን አስልቼ
የምትገኝበት ቦታውን ገምቼ
ፍቅሬን ልገልፅልሽ ልነግርሽ መጣሁኝ
ደምሬ ቀንሸ ሒሳቤን ሰርቼ
በቅቤ ምላሴ ቁልፉን አላልቼ
ሳልሰብረው ልገባ ልብሽን ከፍቼ
ልክ እንዳገኘሁሽ እንደመጣሽልኝ
ልናገር ፈልጌ ቃላቶቹ ጠፉኝ
ብን ብሎ ጠፋ እንደ ወፍ በረረ
የአልጋ ላይ ሀሳቤ ቅዠት ሁኖ ቀረ
ገና አይንሽን ሳዬው መርበትበት ጀመርኩኝ
አንዳች ቃል መተንፈስ መናገር አቃተኝ
የአንደበቴ መዝጊያ ቁልፍ ሁነሽብኝ ።

ብርሃኑ ዘላለም


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19