Get Mystery Box with random crypto!

ለምን ልኑር እኔ ማንን ይድላው ብዬ ልሙት ልውደም እንጂ ይኸው ነው አጣዬ ጤና ይንሳኝ አምላክ በህ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ለምን ልኑር እኔ ማንን ይድላው ብዬ
ልሙት ልውደም እንጂ ይኸው ነው አጣዬ
ጤና ይንሳኝ አምላክ በህመም ልማቅቅ
ከፍታ እያማረኝ ስንኩል ሆኜ ልውደቅ
ጥጋብ ከቶ አይጎብኘኝ
ጠኔ ፀንቶ ያድቅቀኝ
መውደቅ ነው ሚያምርብኝ ለምን ቆሜ ልገኝ
ልጥፋ ከምድረ ገፅ መኖር ምን ሊጠቅመኝ
ኑሮ ብሎ መጥራት 'ላፍ እያሳቀቀኝ
መሞትም መኖርም መብላትም መራብም
መልበስ መታረዝም ማግኘትም ማጣትም
ሁሉ አንድ ከሆነ መለየት ካቃተው
ኑሮ ካሉት አይቀር መቃብር አለም ነው፡፡

Nuniyat
@yetyelele1


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19