Get Mystery Box with random crypto!

አሜን በይ አደራ ያየሽ አይኑ ይጥፋ እግርና እግሩን ያርግበት ወልካፋ። ቡዳ እንደበላዉ ልጅ አይ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አሜን በይ አደራ

ያየሽ አይኑ ይጥፋ
እግርና እግሩን ያርግበት ወልካፋ።

ቡዳ እንደበላዉ ልጅ አይኑ ፈጦ ይቅር አንቺኑ ያየበት
አናቱ ቅል ይሁን አንቺን ያሰበበት
ልቡ ስራ ታቁም ካንቺ የከጀለበት።

ፍቅርሽ እስክመጣ
ፍቅር የተባለ ከወንድ መኖ ይዉጣ
ጠንጋራ ያድርገዉ አንቺን ሊያይ የመጣ።

በፈገግታ ማርኮ ቀልብሽን ለሻተ
ጥርሶቹን አግጥጦ ለተንከራተተ
መጋኛ አግኝቶልኝ ከንፈሩን ያጣመዉ
ጥርሶቹን አርግፎ በድዱ ያስቀረዉ።

እኔ ያንቺዉ መዉደድ ስቃይ እንዳይገባኝ
ቅናት እንዳይገባኝ
ፍርሀት እንዳይገባኝ
ችግር እንዳይገባኝ

የሀገሬዉ ተባዕት በርሀብ ይቀጣ
ሆዱን እያሰበ ወዳንቺ እንዳይመጣ።

የሚበላዉ ይጣ
የሚጠጣዉ ይጣ።
በቃላት ሊያጠምድሽ አንደበቱ ናፍቆ ስምሽን የጠራ
ያሰበዉም ቢሆን ከኔ ፍቅር ጋራ።

ሀረግ ሊደረድር ተፈጥሮ የሰራዉ
ጉሮሮ፣ትናጋ፣ምላስ ከከንፈሩ
ላንቃዉም ሳይቀሩ
የጨዉ ሀዉልት ሆነዉ እዛዉ ደርቀዉ ይቅሩ።

ብቻ ግን አደራ ይሄ ሁሉ ሲሆን
አንዱን አያሳይሽ እንዳይገባሽ ሀዘን
ሲከፋሽ አልወድም።

በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19