Get Mystery Box with random crypto!

፨፨፨ ሰንደቅ~ዓላማ ።።። ከአገራቶች አርማ የቀለማት ውህድ፤ ከትርጉም ቃላቸው የሚስጥራት ሰደድ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

፨፨፨ ሰንደቅ~ዓላማ ።።።

ከአገራቶች አርማ የቀለማት ውህድ፤
ከትርጉም ቃላቸው የሚስጥራት ሰደድ ፤
የጦቢያ ልዩ ነው ቀይ ቢጫ አረንጓዴው ፤
በምድር ከፍታ ላይ ሰማይን ያቆመው፤
የማርያም መቀነት የኖህ ደማቅ ቀለም፤
የአለም አርማ ጦቢያ በሰማይ ማሕተም፤
ወንዙ ቀለም ሳለ ፤እፅዋት ብዕሩ
መጣፊያውም የገፍ ሰማይና ምድሩ
ቀስቱ እየከረረ ፤ደመናን እየሰነጠቀ
በህብር ታጅቦ ፤ቀለም ተሰበቀ
ምነው ለሰውኛ? ያውም ለሃበሻ !
ፀሃይ ያከሰለ አካሉን
የፍጥረት አሃድ አፈሩን
በሰንደቅ ጠቅልሎ
አላማን ሰንቆ አደረገው ጉርሻ ፤
ዝማሬ ተሰቅሎ ጉልበት ሆነ ልምሻ ፤
ምነው? ምነው አንተ-ችየ ?
ሰማችን ቀለለ ክፍተታችን ታየ
ፍቅር ተነቅሶ ፤ልብ ባንድራ አትሮ
ዘላለም ነው አርማ ሰው እስካለ ኑሮ ።

Rebih...


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19