Get Mystery Box with random crypto!

ለ አላዋቂ ሃያሲ በምሁራዊ ስልት በጠቢብ አጫጫር ስንኝን አጣፍጦ በፊደላት ስኳር ቀመሩን አስልቶ ኀ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ለ አላዋቂ ሃያሲ
በምሁራዊ ስልት በጠቢብ አጫጫር
ስንኝን አጣፍጦ በፊደላት ስኳር
ቀመሩን አስልቶ
ኀሣቡን አጉልቶ
ቃላቱን መጥኖ
በድምፆች ከሽኖ
ሐረጋት መስርቶ ያውም አሽሞንሙኖ፤
አላዋቂ ሃያሲ ከረቀ ሰገባው
በንቀት ሲያልፈው ከብዶት ስላልገባው

በአግራሞት ትችት ስለራሱ ሃያሲ
መግጠም ነው መፍትሔው ለግጥም ደራሲ፧፧

ዳዊት ጥኡማይ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19