Get Mystery Box with random crypto!

እረ ማነው እረ ማነው ብርቱ ሞትን የደቆሰ አፈር ያልቀመሰ እረ ማነው የቱ በጥበብ እውቀቱ የቀ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እረ ማነው

እረ ማነው ብርቱ
ሞትን የደቆሰ
አፈር ያልቀመሰ
እረ ማነው የቱ
በጥበብ እውቀቱ
የቀረለት ሞቱ
የትኛው አጥር ነው የትኛው አጃቢ
ሞት የመጣች እለት የሚላት አትግቢ
በመታጠቅ ቢሆን ከሞት መውጫ ዘዴ
ጎልያድም ታጥቋል ሰይፍና ጎራዴ
የጨበጠው ጋሻ መች ከሞት አስጣለው
ዳዊት በወንጭፉ በጠጠር ሲጥለው

አቤል ታደለ