Get Mystery Box with random crypto!

ወዶ አደር (ቶ) --------------------------------- ይገርምሻል አንችየ! አንች | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ወዶ አደር (ቶ)
---------------------------------
ይገርምሻል አንችየ!

አንችን በመጠበቅ
ከአመቴ ቀንሸ ፤
ትመጣለች እያልኩ
ቀናት ጥሎኝ ሸሸ ።

ይገርማል...
አንችን መጠበቁን
ሞት ነው የሚያስጥለኝ
ብየ ስምል፤
ከናፍቆቴ ጋር ሲወዳደር
መሃላየ ይቀላል ።

ይገርማል አንችየ..

አታውቂኝም እኮ
መልኬን አታውቂውም
ቀለሜን አታውቂም
ዘሬንም አታውቂም

ያ ማዶ ነኝ እኔ
እኔ ያንች ጠባቂ
ማነው ከቶ እንዳትይ
ሰው እንዳጠይቂ

እዚህ ማዶም አለሁ
ባካልሽ ላይ ሳለሁ
አንችን በመናፈቅ
አንችን በመጠበቅ
እሞትልሻለሁ ።

ይግረማት መውደዴ..

ሞትን ረትቼ ዳግም ብገኝ
ዛሬም አጠብቃታለሁ
አሷን በመናፈቅ አፈር እሆናለሁ
እሰዋልሻለሁ እጠብቅሻለሁ ።

እይውልሽ አንችየ ለአንች ያጠላውን ጥላቴን ስጠብቅ፤
ሞቱ እያስደሰተኝ በግንባሬ ስወድቅ፤

አካሌ ተሰውቶ ስጋየ ቢመተር
ነፍሴ ወዳ አድራ ነው
........... ስራየ ወቶ አደር ።

Rebih...

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19