Get Mystery Box with random crypto!

ፅልመት ብርት ጥፍት ምጥት ውጥት የሆነ ኑሮ ሆነና ነገሩ ልብህ እና ልቤ መች ተነጋገሩ አንተም | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ፅልመት

ብርት
ጥፍት
ምጥት
ውጥት
የሆነ ኑሮ ሆነና ነገሩ
ልብህ እና ልቤ መች ተነጋገሩ
አንተም እንደዚ ነህ.....
ልክ እንደ ሀገሬ ሙሁር
ሙጭጭ ጥብቅ ነው ባገኘኸው ነገር
ለምን ይመስልሀል........
የመንገዱ መብራት ቦግ እልም እሚለው
አዋቂ ነን ባዬች እየነካኩት ነው
እ....እና
አንተም እንደነሱ ልቤን አታጉላላው
ብዙ ሴት ስላወክ የኔን ልብ አታውቀው
.
.
.
እንባህ ሲንዠረዠር
ከእግርቼ ስር ወድቀህ ስትል ሰለ ፍቅር
አምኜህ ነበረ ልክ እንደ ጨረቃ
ሀዲያ ምን ያደርጋል...
አንተ አደረከው ተመላላሽ እቃ
ከይህ ለጥቆ ግን....
አንተ እንደለመድከው
እየተመላለስክ ልቤን አትነካካው
እኔ እንደው አልሰግድም ለሄደው ለመጣው
አንድ አንተን እንጂ ስልጣንን አልሻው
አሁን
.
.
.
አሁን
.
.
አሁን ግን ልክ እንደ ፅልመቷ
ሊበቃኝ ነው መሰል ካንተጋ ዋይ ዋይታ

ሐና ይመር
Join us
@hanayimer21


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19