Get Mystery Box with random crypto!

ኗሪ እንጂ ሐጅ ቤት አይሰራም (ታደሰ ደምሴ) እየተቃቀፍን አንራራቅ እየተካበርን አንናናቅ ስንቀ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ኗሪ እንጂ ሐጅ ቤት አይሰራም
(ታደሰ ደምሴ)

እየተቃቀፍን አንራራቅ
እየተካበርን አንናናቅ

ስንቀራረብ አንቃቃር
እየተሳሳምን ፊት አንዟር

በልሳን ውበት መካን ይብቃን
ከወረት ጸድተን ፍቅር ይግባን

ባንድ ተኝተን አይብረደን
የበረዶ ማት አያስምጠን

የቃል ሽንገላ ግብር አይሆንም
ኗሪ እንጂ ሐጅ ቤት አይሰራም

የናፍቆት ጅራፍ ካልገረፈን
የትዝታ ወጀብ ካላማታን
የዕምባ ማዕበል ካላጠበን

መለየት ከሆነ ተገናኝተን
የመውደድ ጥጉ መቸ ገባን!

ይልቅ...
ነፍስሽ ከነፍሴ ይወዳጁ
ልብሽ ከልቤ ቀን ይዋጁ

ከየራስ አለም ተሰብስበን
አብረን እንክነፍ ሁሉን ትተን

ያኔ ...
አብረን ስንከንፍ...
የጸሀይ ግለት አያጠቁረን~የብርድ በትር አያጠቃን
በኛ ውስጥ ንግስናን ሽቶ ~ሀገረ ገዢ ንቆ አይደፍረን
"ንጉስሽና ንግስቴ"~ መሆናችንን ችሎ አይነጥቀን!

አዋን...!
አብረን ስንከንፍ...
የሲኦል ነፍሳት ግድ አይሰጠን
የኩነኔ እዳው አያስፈራን

አዎን...
አብረን ስንከንፍ...!
ፈጣሪ ከጽድቅ አይነጥለን
ከፍቅር በላይ ምግባር ሽቶ~ትዛዛቶቹን አይጠይቀን
እኔ ባንቺ አንቺ በኔ ~የገነትን በር እንሾልካለን!
:
:
:
ሹልክ...!

#ሼርርርር
@Maryam21161


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19