Get Mystery Box with random crypto!

ጉድ :::::::::::::::::::::::::::: ሠይጣን መነኮሰ ገዳም ገባ አሉ ከእግዜር ተታረቀ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ጉድ
::::::::::::::::::::::::::::
ሠይጣን መነኮሰ
ገዳም ገባ አሉ ከእግዜር ተታረቀ
ነፍሱን አፀደቀ
ሱባኤ ለሀጥያቱ
ቀኖናዉን ያዘ ለአባ ፍትሀቱ
ሁዳዴን 40ቀን
ሳይታክት ቀን በቀን
እያደገደገ.........
ዳዊት ደጋገመ ሊፀድቅ ወስኖ
ሸይጣን ሰይጣኑ ወጥቶ_ከሰይጣን ተቃርኖ
::::::::::
::::::::::
ሠዉ ሆይ አደራህን እንዳታሳስተዉ
እሱም ብዙ ነበር ካንተ የተማረዉ።


በትዝታ ወልዴ እንደተፃፈ

@Tizita_wolde