Get Mystery Box with random crypto!

በምን ሞተ ቢሉ ህይወት ተገልብጣ እንደ እንትና አብጣ ስር ስታሰቃየው ነው ሞቴን ሞቴን ያለው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

በምን ሞተ ቢሉ

ህይወት ተገልብጣ
እንደ እንትና አብጣ
ስር ስታሰቃየው ነው
ሞቴን ሞቴን ያለው

ወደድኳት ያለን ልጅ ከሱ ርቃ ሄደች
እንኳንስ ልትወደው ሌላ ሰው ወደደች
ፍቅር ቢመረው ነው
ሞትን የተጣራው

ሚወደው ወዳጁ ሲቸገር አልባሹ
ፖተሊካ ብሎ ጊዜውን ወቃሹ
ከጀርባ ወግተውት ወድቆ ከመንገድ ላይ
በፈጣሪ እርዱኝ እያለ ሲሰቃይ
የወዳጁን ስቃይ ማየት ያልወደደው ይሄ ብለቴና
ከሞት ተሽቀዳድሞ ሊያነሳው አለና
አርፎ ስላገኘው
ሞት መቶ ሲቀደመው
ወዳጁን ሲወስደው
ለዛ ነው
ሞትን የተጣራው

ለምን እንዴት ካሉ
ንገሩ ለሁሉ

በህዝቡ ተጠልቶ ሲያገሉት ሰንብተው
ጊዜን ተቀይሞ ይሀው ሞቶ አረፈው።

"በምን ሞተ ቢሉ
ንገሩ ለሁሉ
ሳትደብቁ ከቶ
ከዘመን ተኳርፎ ከዘመን ተጣልቶ"
(ከደበበ ሰይፉ የተወሰደች)

ዮኒ
ኣታን @yonatoz