Get Mystery Box with random crypto!

​​'የኔ ሀገር ሲንኳኳ ፣ ላንተ ሀገር ይሰማል የኔ ቤት ሲቃጠል ፣ ያንተም ቤት ይከስማል፡፡' የ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

​​"የኔ ሀገር ሲንኳኳ ፣ ላንተ ሀገር ይሰማል
የኔ ቤት ሲቃጠል ፣ ያንተም ቤት ይከስማል፡፡"
የሚል የቆየ ሐቅ ፣ ታዲያ ምን ይገርማል?!!

ይልቅ የሚገርመው ፣ ይልቅ የሚደንቀው
የኔ ቤት ሲቃጠል ፣ ያንተ ቤት ከሞቀው፡፡

ይልቅ የሚገርመው ፣ የሚደንቀው ነገር
ያንተ ሀገር ሲንኳኳ ፣ ካልተሰማ እኔ ሀገር
ወይ ተሰድጃለሁ ፣
ወይ አውቆ ተኚ ነኝ ፣ ወይም አለ ነገር።

[ በላይ በቀለ ወያ ]