Get Mystery Box with random crypto!

ታሪክ ምን ይለናል? ታሪክ ምን ይለናል መለስ ብለን ብናይ ምንስ ይነግረናል እኮ ምን ይለናል? አ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ታሪክ ምን ይለናል?

ታሪክ ምን ይለናል
መለስ ብለን ብናይ ምንስ ይነግረናል
እኮ ምን ይለናል?
አደዋ ምንድነው
ለማን ነው የታገለው
ለኔ ለአንተ አደለም
ቀኝስ ያልተገዙት ለኛ አደለምን?
እስኪ ልጠይቅህ
እንዳታሳፍረኝ ሰብሰብ በል ከራስህ
ጣልያን ሲወረን ሲከፍትብን ጥይት
ማን ነበረች ያቺ ከፊት ተሰልፋ ያርበደበደችው የሴቶቹ ጀግኒት
ጠይቀሽ ሞተሻል አያውቅም ብለሽ ነው
እኮ እነማን ናቸው ንገረኝ ከነ ማዕረጋቸው
እንኳን እኔ እና አለም ያውቃቸዋል እትዬ ብርጣሉ አምርብር አደሉ
እንዴት ያለ ታሪክ አውቀኸልኝ ኖራል
የኔ ባቶን ኖሮ እንዴት ይቆጨኛል
ፍረጅኝ አንቺ አገር
ታዲያ እንዴት ብዬ ስላንቺ ልናገር
ከአፈርሽ የወጣው ልጄ የምትይው
ታሪክ ባህልሽን እንዲ እያዛባው
ንገሪኝ ሀገሬ ምን ተሰምቶሽ ይሁን
ሀዘኑ መጥፎ ነው ይጎዳል ውስጥሽን
አዋይኝ ለልጅሽ አታልቅሽ ብቻሽን
አንዴ ባጋጣሚ ገባው አዝማሪ ቤት
እንዲ ሲል ተቀኘ ሆድ አንጀቴን በልቶት
እናት የሞተ እንደው
በሀገር ይለቀሳል
አባት የሞተ እንደው
በሀገር ይለቀሳል
ዘመድ የሞተ እንደው
በሀገር ይለቀሳል
ሀገር የሞተ እንደው
በምን ይለቀሳል
እንባዬ በጉንጮቼ ወርደው አንገቴን አልፈዋል
ስለ ሀገር ሲነሳ ሆዴን ይብሰኛል
ግን
ግን
እንደ አንተ አይነቱ
ስንቱን ያሰድባል ሆኖ የሰው ከንቱ
እኔ ግን ልምከርህ
ትውልዱ ከሰማህ
በውጭ ሀገር ታሪክ ናላህን ስታዞር
የራሳህ ታሪክ መሪውን እንዳያዞር

ሐና ይመር


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19