Get Mystery Box with random crypto!

ከሌላ ሰው መጽሐፍ የተቀነጨበ ከህመሞች ትልቁ ህመም ካንሰር ወይም ኤድስ ሊመስለን ይችላል። እውነ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ


ከሌላ ሰው መጽሐፍ የተቀነጨበ

ከህመሞች ትልቁ ህመም ካንሰር ወይም ኤድስ ሊመስለን ይችላል። እውነቱ ግን እንደ ስብእና መዛባት የከፋ ህመም የለም። ውጫዊ መልክ የሰው የገጽ ሽፉን ነው።

ስብእና ግን የሰው እውነተኛ መልክ ነው።
በየእለቱ አብረን የምንኖረው ሰው እውነተኛና የማያረጅ ዘላቂ ማንነታችን ስብእናችን ነው።

በአይናችን የማናየው እውነተኛ መልካችን
በውስጥ ማንነታችን ውስጥ ተቀብሮ ያለው ስብእናችን ነው። የስብእና ስንኩልነት ፣ ጠባሳዎችና መዛባቶች ቤት ያፈርሳሉ፤ አገር ይንዳሉ፤ ግንኙነትን ይመርዛሉ። ለማከምና ለማዳን ብቻ ሳይሆን ለማየትና ሕመሙን ለመረዳትም አዳጋች ነው።

ስብእና በልጅነት እንደ ተቦካ ሲሚንቶ ፣ በአዋቂነት ደግሞ እንደ ደረቀ አርማታ ነው።
የብዙ ሰው ስብእና እንደ ተቦካ ሲሚንቶ በልጅነቱ በትክክል የሚቀርጸው ካላገኘ ተንሻፎና ተዛብቶ ያድጋል። እድሜው ከገፋ በኋላ ደርቆ ስለሚጠነክር ፣ ብዙ ጊዜ ለምክራ መዶሻና ለምክር መጥረቢያ አዳግቶ አገር ያጠፉል።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19