Get Mystery Box with random crypto!

አይሆንብሽም ብዬ ነበረ አንቺ ላይ ይ ሁሉ መከራ ግፍ እና ስቃይ እምነት ነበረኝ ሰላም ሆነሽ እን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አይሆንብሽም ብዬ ነበረ አንቺ ላይ
ይ ሁሉ መከራ ግፍ እና ስቃይ
እምነት ነበረኝ ሰላም ሆነሽ እንደማይ
መራብ መጠማቱ አንድነት ማጣቱ
እርስ በራስ መባላቱ አንዱ አንዱን ማጥፍቱ
መተሳሰብ ቀርቶ በቂም መሞላቱ
አንድነቱ ርቆ ጭካኔ መብዛቱ
በጨካኞች እጅ ሰው ሲታረድ አንገቱ
ምን ሰውን ብቻ ሳይቀር እንስሳቱ
ይህን ሁሉ ግፍ አቃተኝ ማየቱ
ሌላ ኢትዮጵያ አሰኘኝ በውነቱ
በምናብ እማቃት በየ መጽሐፍቱ
ያቺ የሰፈረች በመጽሐፍ ቅዱስ
እጆችዋን ወደ ላይ ሁሌም እምታደርስ
እንግዳ ተቀባይ በጣም የምትል ደስ
ሁሉም የሚመኛት መንፈስ የምታድስ
እቺን ኢትዮጵያ ሁላችን እንድናይ
ያቺን አሳልፈን ከዚች እንድንወያይ
እባካችሁ ሰዎች እንጸልይ ወደላይ


ዮናስ ጌታሁን


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19