Get Mystery Box with random crypto!

ብቻ አንቺ አርፍጂ እንጂ ቁና በማትሞላ በዚች በኛ ሰፈር እንቅብ ሙሉ ቆሎ ይዞ እንደሚዞር እንደ ቆ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ብቻ አንቺ አርፍጂ እንጂ
ቁና በማትሞላ በዚች በኛ ሰፈር
እንቅብ ሙሉ ቆሎ ይዞ እንደሚዞር
እንደ ቆሎ አዟሪ
እጠብቅሻለሁ ዞሬ ዞሬ ከዛው
ቆሎ እየሸጠ ቆሎ እንደሚገዛው

ብቻ አንቺ አርፍጂ እንጂ
እጠብቅሻለሁ እንደ ሴት ልጅ እድሜ
አልንቀሳቀስም ካለሁበት ቆሜ

ብቻ አንቺ አርፍጂ እንጂ
እጠብቅሻለሁ እንደ ቀትር ጸሃይ
እንደ መከራ ቀን እንደ ክረምት ሰማይ
ይዞ እንደማይለቃት እንዳገሬ ጉንፋን
ዘመን የማይነቅለው እንደ እግዜሩ ዙፋን

ብቻ አንቺ አርፍጂ እንጂ
እጠብቅሻለሁ እንደ ድህነቴ
ቀናት እያለፋት
ዘመን እየገፋት በዘመመች ቤቴ

ብቻ አንቺ አርፍጂ እንጂ
ሰላም ጦርን ሲያክም
እንደ ኩሊ ጀርባ ቀና ሲሉ ሸክም
በሆነባት ሃገር
እጠብቅሻለሁ እንዳሮጊት ጫማ
የመምጣትሽን ኮቴ ጆሬዬ እስኪሰማ

ብቻ አንቺ አርፍጂ እንጂ
ተስፋም ተስፋ ያደርጋል ይነጋል በሚል ቃል
በዚች በኛ መንደር፤
ያገር ትንሳዔና ያረፈደች ወጣት እኩል ይጠበቃል

@Dagim_dagii


ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19