Get Mystery Box with random crypto!

በስሜት ቸኩለን መሻር ፥ ቸኩለን መሾም አይበቃንም ወይ ፥ አፍሶ መልቀም የቆምንባትን ፥ የሀገር | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

በስሜት

ቸኩለን መሻር ፥ ቸኩለን መሾም
አይበቃንም ወይ ፥ አፍሶ መልቀም

የቆምንባትን ፥ የሀገር መርከብ
እንዳናሰምጣት ፥ በስሜት ወጀብ

በሀሰት ትርክት ፥ በእቶ ፈንቶ
የፈሰሰው ደም ፥ ፅዋውን ሞልቶ
ነገን እንዳናይ ፥ ከዛሬ ከፍቶ

በስሜት ንፋስ ፥ እየዘወርናት
ከአምላኳ ጋራ ፥ አቀያይመናት
ወጣቱን ማግደን ፥ ለጥይት እራት
ለእሳት ማገዶ
ዓሳ ስናልም ፥ እንዳናይ ዘንዶ


አቤል ታደለ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19