Get Mystery Box with random crypto!

ንገሯት ንገሯት ለዛች ሰው ጥላው ለሸፈተች መልክ አይኗን ሳይጠግበው | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ንገሯት

ንገሯት ለዛች ሰው
ጥላው ለሸፈተች
መልክ አይኗን ሳይጠግበው
ሄዳ ላከተመች
ርቃ ለቀረች
ሞቶልሻል በሏት
ሀዘን ከተሰማት
ይሉኝታ ካጠቃት
መሞቱን ንገሯት

ታድያ ስትመጣ....

ባታፈቅረው እንኳ ጥቁር ነገር ትልበስ
ለታይታውም ቢሆን ፊቷ አመድ ይልበስ
ያኔ እንዲ በሏት
"በተፈጥሮ ተችሮት አንቺን አፈቀረ
ሟች ከመሞቱ በፊት ያፈቅርሽ ነበረ"

.......
ኣታን።

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19