🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ነጻነት ነጻነትን ስንመኝ ፤በባርነት ሆነን ነጻነት በነጻ፤ መፈለግ ጀመርን ዳሩ ግን አጣነው ፤ቀረ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ነጻነት
ነጻነትን ስንመኝ ፤በባርነት ሆነን
ነጻነት በነጻ፤ መፈለግ ጀመርን
ዳሩ ግን አጣነው ፤ቀረ እንዳማረን
ለካ ነጻነት፤ ዋጋ ያስከፍላል
ደምን ያስፈስሳል፤ ሞትንም ያስሞታል
አንዱ ቆሞ እንዲሄድ፤ አንዱ ይገደላል
ያኔ ሰይጣን አስሮን፤ በአዳም በደል
ፅድቅም ሰራን ሀጥያት ፤ መወርወራችን ነው ወደ ሲኦል ገደል
ከሲኦል ለመውጣት፤ እስቲ ማን ይክፈል
የኛን ስቃይ አይቶ፤ የኛን መገደል
ክርስቶስ ሲደማ፤ እሱ ሲገደል
እኛን ከሲኦል አውጥቶ፤ አረገ በድል
ዛሬም ለኢትዮጵያ መቆም መቀጠል
ወታደራችን ነው ሳይፈራ እሚጋደል
ምንም ሳይበግረው በዱር በገደል
ስለዚ አስባቸው ሁሌም አስታውሳቸው
የነፃነት አርማ ባንዲራ አድርጋቸው

ዮናስ ጌታሁን

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19