🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ቃላት አጣውላት ከእስክሪብቶ ጫፍ ላይ ፤ በሚወጣው ቀለም ብሶቴን ልወጣ ፤ ህመሜን ለማከም በነጩ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ቃላት አጣውላት

ከእስክሪብቶ ጫፍ ላይ ፤ በሚወጣው ቀለም
ብሶቴን ልወጣ ፤ ህመሜን ለማከም

በነጩ ወረቀት ፤ ከሸንጎ ገትሬያት
በብእሬ ቀለም ፤ ሄዋንን ከስሻት
በቃላት ካቴና ፤ በግጥሜ ላስራት

ከኦረት ዘፊጥረት ፤ እስከ ራዕይ ድረስ
ወንጀሏን ለቅሜ፤ ከመፅሀፍ ቅዱስ

በገላዋ በውበቷ
በቀጭኑ አንደበቷ
የሄዋን ልጅ የሲፖራ
የአዳምን ልጅ ልብ አውራ
ያመጣችበትን አበሳ
በብእሬ ላወሳ

የግጥሜን እስር ቤት ፤ በፊደል ልቆልፈፍ
መያዙአን ሳስታውስ ፤ እናት የሚባል ቁልፍ

ድካሜ ልፋቴም ፤ ሆነብኝ ስንፍና
ቤት የሚመታልኝ ፤ የቃላት ካቴና
እናት በሚባል ፤ ቁልፍ ይከፈታልና


አቤል ታደለ

ከወደዱት ለወዳጆ ያጋሩ
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19