Get Mystery Box with random crypto!

ርዕስ የለውም............ ያኔ ጦርነት ሳይከበን ሳይከፋፈል ሀገር እኔ ካንቺ ሳርቅ አንቺም | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ርዕስ የለውም............

ያኔ
ጦርነት ሳይከበን ሳይከፋፈል ሀገር
እኔ ካንቺ ሳርቅ
አንቺም ሳትርቂ እንዋደድ ነበር
ጊዜ ጊዜን ወልዶ ሰፋና ነገሩ
አንቺም ከሌላ ሰው ኪዳን አሰርሽ አሉ።

ያኔ ልጆች ሁነን
በቁርባን ተጋብተን
ብዙ ሃብት አካብተን
2..3..4..ወይም ደርዘን
ልጆች አንወልዳለን ተባብለን ነበር።

ቀን ቀንን ሲወልደው ሲሻገሩ አመታት
በአባቶቻችን ጠብ ቀረብን ለቅጣት
ያነ ሁሉ ጊዜ...ያ ሁሉ ዝማሬ
ለካ ለዚ ነበር
ምነው ባላወኩሽ ልንለያይ ነገር...

ጥቂት አመት በፊት በተስኪያን ተሳልመን
በዘንባባ ቅጠል
ያለ ሽማግሌ ኪዳናችን አስረን
ላልለይሽ ቃል ገባው
ላትለይኝ ቃል ገባሽ
ታቦታትን ጠራው
ታቦታትን ጠራሽ
ጊዜ ጣለንና
ዛሬ ተለያይተን አንቺም ሌላ አገባሽ።

ስሚኝ ይኸውልሽ
አንድ ላይ እያለን እንዋደድ ነበር
ምትለዋ ስንኝ ታጠራጥረኝ ጀመር
ብንዋደድ ኑሮ...
ስሟ ተጠርቶ እንኳ ማትጠገብ ሃገር
ዘር ምክንያት አድርገን አንጣላም ነበር. ...

በዘር ተመስርቶ ፍቅር ከጀመረ
የሃበሻነት ደሙ እንዲህ ከባከነ
ፍቅር ድሮ ቀረ።
ያብሮነት ህግጋት ተሻረና ውሉ
አንቺም ከሌላ ሰው ኪዳን አሰርሽ አሉ።

ዮኒ
ኣታን @yonatoz