🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በቀልና ፍንጥርጣሪው ክፍል 37 ፀሃፊ ሸረፈዲን የእናቱ ልጅ . . . እንደ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

በቀልና ፍንጥርጣሪው
ክፍል 37
ፀሃፊ ሸረፈዲን የእናቱ ልጅ
.
.
.
እንደነጋለት ሚኪ ቢሮ ገብቶ ከጥቂት ቀን በፊት ያዘጋጃቸውን ሰነዶች ማስተካከል ያዘ። ልቡ ግን ልትረጋለት አልቻለችም መኩሪያው ያቺን አንድ ፍሬ ልጅ የደፈረበት ሁኔታ ከእናቱ አደፋፈር ጋር ተመሳሳይ ነው ልክ እንደ እናቱ ሁሉ እቺም ልጅ እጆቿ ታስረዋል.. እግሮቿ ወዲያና ወዲህ ተበርግደው ተጠፍንገዋል።... ሚኪ ልጅቷን እያሰበ ውስጡን በረደው።...
"መኩሪያው አብቅቶልሃል...እጅግ በሚያምኑት ሠው መከዳት ምን ያህል እንደሚያም ዛሬ ይገባሀል" አለና ለሮቤል ስልክ ደወለለት...
"ሄሎ ሮቤል....ልጅቷን አገኛችሁዋት.... ?" አለው ሚኪ ስለ ደህንነቷ ለማረጋገጥ
"አዎ ሚኪ ግን እሥካሁን አልቀረብናትም....የመኩሪያው ሠዎች አምጥተው ጉሊት ወርውረዋታል...እናቷ ልጇን ታቅፋ እያለቀሠች ነው። ጥቂት የማይባሉ ሰዎች ስላሉ ፓሊስ ጉዳዩ ላይ ከገባ ብለን ነው እሥካሁን ምንም ያላደረግነው...
"ልጅቷ ተጎድታለች እንዴ...?"
"አዎ በጣም የተጎዳች ትመስላለች ደክማለች"
"እና ሮቤል ምንድነው የምጠብቁት ይዛችሁዋት ሆስፒታል ግቡሃ.....ህይወቷ እያለፈ ሥለምን ፓሊስ ነው የምታወራው"
"እሺ እንዳልክ" አለው ሮቤል
"እባክህ ሮቢ ፍጠኑ..እኔ መኩሪያው ጋር ያለኝን ጉዳይ ጨርሼ እመጣለሁ" ሚኪ ስልኩን ዘጋውና በዝምታ ለጥቂት ጊዜ ለማሰብ ሞከረ።....
ልክ ከጠዋቱ 5 ሰአት ሲል ወረቀቶቹን ይዞ ወደ መኩሪያው ቢሮ አመራ.....ሚኪ አምስት ሠአትን የመረጠው የሁልጊዜ የመኩሪያው ከስራ የመውጫ ሰአት በመሆኑ ነው....ያሰበው ነገር ደግሞ ሊሆንለት የሚችለው መኩሪያው ለመውጣት እየተጣደፈ ባለበት ጊዜ ነው።.....
ሚኪ ቢሮውን አንኳኳ....
"ይግቡ" አለ መኩሪያው....
"ጋሼ ሠላም ነዎት ...እንዴት ነው ለበረራው ተዘጋጁ....?" አለ ሚኪ በቆመበት...
"አዎ ተዘጋጅቻለሁ...እንዲያውም ልወጣ ሥል ነው የመጣኸው..ቤት ሂጄ ትንሽ እረፍት ማድረግ አለብኝ" አለ መኩሪያው ወንበሩ ላይ ለጠጥ ብሎ.....
ሚኪ እሥከዛሬ ሲያየው ከሚይናድደው እጥፍ ድርብ አሁን በጣም እየተቃጠለ ነው ነገር ግን ያስበውን ለማሳካት መተወን የውዴታ ግዴታው ነው ..
"ብዙ ጊዜ አልወሥድብዎትም ጋሼ እቺን ወረቀት እንዲፈርሙ ነው.."
"ምንድነው....?" አለ መኩሪያው መነጸሩን ከፍ ዝቅ እያደረገ
"አዲስ ምርቶችን ከሚያቀርብልን ድርጅት ጋር የተዋዋልነው ውል ነው.....እርስዎ ለአንድ ወር ስለሚቆዩ ስራው መጓተት የለበትም ብዬ ነው ሳይሄዱ በፊት ቀድሜ ላስፈርመዎት የመጣሁት"
"አንበሳኮ ነህ የኔ ልጅ...ምነው እንዳንተ አይነቱ ታታሪ ድርጅቴ ውስጥ ሶስት አራት ቢሆንልኝ...ስጠኝ ወረቀቱን ልጄ" አለው መኩሪያው በመደሰት...
ሚኪ ወረቀቱን አቀበለውና መኩሪያው ሳያነብ እንዲፈርም ለአምላኩ ጸሎት ማድረስ ጀመረ...
መኩሪያው ወረቀቶቹን እየገለጠ ያለምንም ጥርጣሬ ይፈርማል..ሚኪ ሳቁ ሊያመልጠው ምንም አልቀረውም......
መኩሪያው ሁሉም ወረቀቶች ላይ ፈርሞ አቀበለው....
"መልካም ጉዞ" አለው ሚኪ ለመውጣት በሩን እየከፈተ....
"አመሰግናለሁ . .ቆይ ልጄ አንዴ" አለው መኩሪያው
ሚኪ ፊቱን መለሰ "ልጄ የውክልና ወረቀት ስላስገባሁ እሥክመጣ ወክለኸኝ ድርጅቱን ትቆ ጣጠርልኛለህ.....ማንኛውንም ነገር ለማከናወን እኔ አላስፈልግህም በራስህ ማድረግ ትችላለህ" አለው መኩሪያው...
"አያስቡ ጋሼ እርሥዎ እንዳዘዙ" ሚኪ ቢሮውን ለቆ ወደ እራሱ ቢሮ ገባና ከውሥጥ ቆለፈው....
ተሽከርካሪው ወንበር ላይ ተቀምጦ ዝም ብሎ ይስቅ ጀመር ካካካካ ብቻውንም ያወራል።
"አይ መኩሪያው ምን አይነቱ ጅል ነህ በፈጣሪ ድርጅትህን ካለምንም ችግር በቀላሉ በገዛ ጣቶችህ ፈርመህ ሰጥተኸኝ ውክልና ምናምን ሠጠሁህ ትላለህ ካካካካካ ሲጀመር ምን ድርጅት አለህና ወሠድኩብህኮ ካካካካ"
ሚኪ መልሶ ደግሞ ይናደዳል...ወደ ነብርነት ይቀየራል
" መኩሪያው እንዲያውም እንዳንተ ጨካኝ ባለመሆኔ አመስግነኝ...አንገትህን አላረድኩትም ወይም ቤተሠብህን አልጎዳሁትም" አለ ሚኪ ጠረጴዛውን በእጆቹ ተደግፎ እራሱን በመስታወቱ ትኩር ብሎ እያየ....
"እቺ ቀን ልጅነቴ ነች..እቺን ቀን ለማግኘት ልጅነቴን አጥቻለሁ....ዛሬ የመደሠቻዬ ቀን ነው ለምን አዝናለሁ።...አባዬ ንብረትህን አስመልሻለሁ አሁን ነፍስህ በሰላም ታርፋለች በልጅህም ትኮራበታህ። ጥቂት ቀን ብቻ ጠብቅ መኩሪያው በህዝብ ፊት ተዋርዶና ተንቆ ዘብጥያ ይወርዳል" አለ ሚኪ ድምጹን ዝቅ አድርጎ ከዋሌት ኪሱ ያወጣውን የአባቱን ጉርድ ፎቶ አዘቅዝቆ እያየ።
ሚኪ ቢሮውን ቆለፈና ተጠቂዋን ልጅ ለማየት እነ ሮቤል ያሉበት ቅዱስ ጳውሎስ ሆስፒታል ሄደ።
እንደደረሰ ልጅቷ በቂ ህክምና እየተደረገላት ነበር... ሮቤል፤ሂዊ፤የልጅቷ እናት እንዲሁም የሠፈሩ ሰዎች የድንገተኛ ክፍሉን በራፍ ከበው ቆመዋል።
ሚኪ እነ ሮቤል ጋር በማምራት "ልጅቷ እንዴት ናት.....?" አላቸው የማንሾካሾክ ያህል
"ደህና ትሆናለች ብዬ አሥባለሁ" አለው ሮቤል...
"ምን ማለት ነው ይሄ ለህይወቷ ያሰጋታል እንዴ....?" ሚኪ በድጋሜ ጠየቀ...
"አናውቅም ዶክተሩ መጥቶ ምንም አላላንም" ሂዊ መለሰችለት
"ምንድነው የያዝከው ወረቀት" አለው ሮቤል...
"ሂዊ.. ሮቢ"...አደረኩት አላቸው ሚኪ ገለጥ አድርጎ እያሳያቸው...
"በቃ ቤት ስንደርስ በዝርዝር እናወራበታለን።" አለው ሮቤል..
በመሀል ዶክተሩ ከድንገተኛ ክፍሉ ወጣ....ወሬያቸውን ትተው ወደ ዶክተሩ አመሩ.....
እናቷ "ልጄ እንዴት ናት ዶክተር..?" አሉት እያለቀሱ...
"አይዞዎት ደህና ናት....ግን በወንድ ጥቃት ደርሶባታል.."
"ምን ማለትህን ዶክተር...እንደው ምና አድርጋቸው የኔን ሚስኪን ልጅ ይደበድቧታል" አሉት
"ማዘር አዝናለሁ ይሄን ስልዎት ግን ማወቅ አለበዎት ልጅዎት ተደፍራለች" አላቸው
"እግዚኦ...እግዚኦ ልጄን አንድ አይኔን ጉድ ሠሩኝ...ልጄን ቀሙኝ" እናቷ ሆስፒታሉን በጩኸትና በእዬዬ አደበላለቁት....
"ማዘር ይረጋጉ አሁን ላይ በህይወት አለች..
መድሀኒቶች ሠጥተናታል ከግማሽ ሠአት በሁዋላ ትነቃለች.....ስለዚህ እንዲህ አይሁኑ" አላቸው ዶክተሩ
ሚኪና ሂዊ እናትዬዋን ደግፈው እንዲረጋጉ ጥረት አደረጉ...
ሮቤል ግን ዶክተሩን ተከተለው...
"ዶክተር አንዴ ቆይ" አለው ሮቤል
"አቤት..."
"ልጅቷን እናቷ ይዘው ሲያለቅሱ አይተን እኛ ነን ከመንገድ ይዘናት የመጣነው..አሥፈላጊውን ወጪ እኛ እንሸፍናለን" አለው ሮቤል
"ተባረኩ ሠውን መርዳት የሚችሉት ጥሩ ልብ ያላቸው ብቻ ናቸው...." ብሎ መለሰለት ሽበት የወረረው ዶክተር
"ዶክተር ያው ቤተሠብ ስላልሆን ልጅቷን ማየት አይፈቀድም ይሆናል ግን ሁኔታዋን አይተን አሥፈላጊውን ነገር እንድናሟላላት ገብተን ብናያት ብዬ አሥባለሁ...ሥለዚህ ልትፈቅድልን ትችላለህ...?"
"ችግር የለውም እተባበራችሁዋለሁ...ከአንድ ሠአት በሁዋላ ልታዩዋት ትችላላችሁ..እንዲያውም እያሰብኩ ያለሁት ምን መሠለህ አካላዊ ቁሥሏ በጥቂት ቀናት ውስጥ ይድናል ግን ሥነ ልቦናዋ ሊቃወሥ ይችላል ብዙ ጊዜ እንደሷ አይነት ተጠቂዎች እራሳቸውን በቶሎ ማግኘት አይችሉም ስለዚህ ከዚህ ስትወጣ የስነ ልቦና ሀኪም ጋር ብታሳዩዋት ጥሩ ነው.." ዶክተሩ የመፍትሄ ሀሳብ ያለውንም እግረ መንገዱን አክሎ ነገረው...
"እሺ ዶክተር እናመሰግናለን"...
ልጅቷ ከግማሽ ሠአት በሁዋላ ነቃች...እነ ሚኪም በተፈቀደላቸው መሠረት ከአንድ ሠአት በሁዋላ ሊያዩዋት ገቡ.......