🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​ልጅቷ ስታያቸው ተረብሻ ነበር....የመኩሪያው ሠዎች መሥለዋት እጅግ ፈራች ነገር ግን እናቷ እየ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

​​ልጅቷ ስታያቸው ተረብሻ ነበር....የመኩሪያው ሠዎች መሥለዋት እጅግ ፈራች ነገር ግን እናቷ እየረዷቸው እንደሆነ አ ሳምነዋት ተረጋጋች።....
እነ ሚኪ ትንሽ ከተጨዋወቱ በሁዋላ የ20000 ብር ቼክ አበርክተውላቸውና ችግር ከተፈጠረ ሥልክ እንዲደውሉላቸው ሥልካቸውን አሥቀምጠውላቸው ወደ ቤታቸው አመሩ።.....
ወደ ቤት እንደገቡ ሚኪ ሊያስቀምጣቸው እንኳን አልቻለም "መኩሪያውን በቁሙ ቀበርኩት" እያለ ወረቀቱን ሰጣቸው......
"omg ላንተ ደስ ብሎኛል" ሂዊ ጉንጩን ሳመችው
"አደርገዋለሁ ካልክ እንደምታደርገው አውቅ ነበር ኮርቼብሃለሁ ጓደኛዬ" ርቤል ጠበቅ አድርጎ አቀፈው.....
"አመሠግናለሁ ጓደኞቼ...እሺ አሁን ምን እናድርግ....ፈጣን እርምጃ እንውሠድ ወይሥ.....?" አለ ሚኪ
"እንደኔ ብንረጋጋ ይሻላል ባይ ነኝ....በእርግጥ አሁን ያለን መረጃ መኩሪያውን ያስፈርድበታል ችግሩ ግን ድርጅቱ ውስጥ ያሉበት ባለስልጣንስ ነው...? መኩሪያው ቢታሰር ሌላኛው ይተካል መኩሪያውን ከእሥር ለማውጣት አንድ ዘዴም አያጡም.."
"እና ምን ይሻላል..?" አለች ሂዊ
"የሚሻለውማ ችግሩን ከላይ ሳይሆን ከስር እንንቀለው....ጭራሽኑ እናጥፋው ነው እያልኳችሁ ያለሁት.. ወንጀሉን ለማሥቆም መኩሪያው ጋር ሲሰሩ የነበሩትን እያንዳንዱን ባለስልጣን ቅጣታቸውን እንሥጣቸው ነው"...
"ግን እንዴት....መረጃው የት እንደገባኮ አናውቅም ደብዛውን አጥፍተውታል....ኮማንደሩን እንኳን መለየት አልቻልንምኮ" አለ ሚኪ ሁሉም ነገር ተዘጋግቶበት..
"እኔ አንድ ሀሳብ አለኝ...ሀሳቤ እርግጥ ከሆነ" አለ ሮቤል ጺሙን እያሻሸ
"ሮቢ ተሳስተህ አታውቅምኮ ንገረንና እንሞክረው" አለችው ሂዊ ፈገግ ብላ
ሮቤል በሂዊ አፍ መሞገሱ እያስደሰተው ንግግሩን ቀጠለ "የመኩሪያውን ቤት መፈተሽ አለብን!" ሮቤል መፍትሄውን አሥቀመጠ
"የትኛውን...ሴቶችን የሚያባልግበትን ነው.....?" ሚኪ ጠየቀ
"አትሳሳት ሚኪ ወንጀለኞች ድብቅ ነገራቸውን ሁሉም ሰው የሚያየውና የሚያውቀው ቦታ ነው የሚያስቀምጡት ምክንያቱም ሰው የለመደውን ቦታ ማንም አካል ትኩረት እንደማያደርግበት ጠንቅቀው ያውቃሉ.....ስለዚህ ትልቁ መኖሪያ ቪላው ውስጥ ነው ሊደብቀው የሚችለው....እድል ከቀናን ቢሮው ውስጥ ወይም ልክ እንደኔ የሚስጥር ክፍል ይኖረዋል"
"የሚገርም ሀሳብ....እኔ በማንኛውም ሰአት ዝግጁ ነኝ...መች እናድርገው" አለች ሂዊ...
"በደንብ አቅደንበት እናደርገዋለን" ሮቤል መለሰላት....
ሁሉም ትልቁ መኖሪያ ቤት ያለውን ቢሮውን ለመበርበር ተ ስማምተው ተለያዩ።

ሚኪ ቤቱ ደርሶ ብቻውን ማሰብና አረፍ ለማለት ስለፈለገ ሂዊን መንገድ ላይ አውርዷት ወደ ቤቱ ገሰገሰ......ቤቱ ደርሶ በራፉን ለመክፈት ሲሞክር ግን በራፉ አልተቆለፈም በሰውነቱ ሲታከከው በራፉ ተከፈተ...
ሚኪ የባለፈውን ስህተት ላለመድገም ሽጉጡን አወጣና ቀስሮ ዙሪያ ገባውን እየቃኘ ወደ ውስጥ ገባ ነገር ግን ፊት ለፊቱ በፍጹም ያልጠበቀውን ነገር ተመለከተ
ሰላም ቀኝ እግሮቿን አነባብራ ሶፋው ላይ ተቀምጣለች....የጭንቀቱን እጁ ላይ ያለውን ሽጉጥ ለመደበቅ ተውተፈተፈ........
"ለመደበቅ አትሞክር" አለችው
"እእእ ሰላሜ" ብሎ ሲጠጋት ቅድም በድንጋጤ ያላየው የአባቱ ፎቶ በሰላም እጅ ላይ ተንጠልጥሎ ተመለከተው።
ከአይኖቿም እምባ እየፈሰሰ ነው..

ይቀጥላል
Share Share Share
ከወደዱት ሼር ያድርጉ
@bewketuseyoum19