🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ከሰማይ ላይ ተስለሻል ደመናውም ይመስልሻል ፀሐይ ካንቺ ተስተካክላ ሕይወት አንቺን አስመስላ ጥርስሽ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ከሰማይ ላይ ተስለሻል
ደመናውም ይመስልሻል
ፀሐይ ካንቺ ተስተካክላ
ሕይወት አንቺን አስመስላ
ጥርስሽ ፀዳል እየረጨ
ፊትሽ ጮራን አመነጨ
የሄድሽበት ሳር ቅጠሉ
ማማር ሆኗል እጣ እድሉ
የረገጥሽው መሬት ምድር
መፍካት ማበብ መድመቅ ክምር
ከጎዳናው የወጣሽ ለት
ካደባባይ የታየሽ ለት
ወንዱ አቅሉን እየሳተ
ሴቱ ገላ እየጎተተ
አበቦቹ እየፈኩ
እንስሳት እየረኩ
ሰማይ ምድር እያውካኩ
ሕይወት ከሞት ሲነካኩ
ሰይጣን ግብሩን ሲዘነጋ
የውበትሽ ሀያል መንፈስ እሱን እንኳን እያላጋ
መላእክታት ሲገረሙ
በአድናቆት ሲያረምሙ
አውሎ ንፋስ ሲነሰነስ
ሰማይ ምድር ሲቅለሰለስ
አይቻለሁ ሀያል መንፈስ
የውበት መናፍስት የቁንጅና ጌታ
ከአንድ ከትመው ባንቺ ወገን ተርታ
ወንዱ ብቻ ሳይሆን ተፈጥሮም ተረታ
ከሰማይ ላይ ተስለሻል
ደመናውም ይመስልሻል
ሰማይ ምድር አፍቅሮሻል
ይሄ ሁሉ ያንስብሻል።


አክሊሉ ተስፋዬ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19