Get Mystery Box with random crypto!

ፀሎት አድራሽ ፈለኩ፣ ሰንፌ አይደለም፣ እመኚኝ ግድ የለም፣ ምልጃዬን ተረኩት፣ አጀብ ተባለልኝ፣ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ፀሎት አድራሽ ፈለኩ፣
ሰንፌ አይደለም፣
እመኚኝ ግድ የለም፣

ምልጃዬን ተረኩት፣
አጀብ ተባለልኝ፣
መንደርቴ ሲሰማ በቁሜ ለየልኝ!

ይቺ ናት ፀሎቴ፣
አድራሽ የምትሻ፣
ማትከብድ ለትከሻ!
የነገርኩት ሰማ ይቺን ፀሎት ብሎ፣

"መጨረሻዋን አስጀምርልኝ"

የወፈፌ፞፞፞ ፅንፉ ንገሪኝ ምን ይሆን?
እኔ ግን አላብድም፣
አላብድም ሰው ልሆን!
የሆንኩት እንዲህ ነው፣
ያልሆንኩትን እንጃ፣
ሰምተሽ ትሰጫለሽ “አብዷል” የሚል ፍርጃ!
.
.
«..ሲያለቅሱ ሳኩ እንጂ ሲስቁ አልሳኩም፣
«..ሱሪ ባንገት እንጂ በ'ግር አልሞከርኩም፣
«...ውሀ ፈራሁ እንጂ ምግብ አልፈለኩም፣
«..እርቃኔን ሄድኩ እንጂ ሽፋን አለበስኩም፣
«..አንቺ'ኳ ተረጂኝ እኔኮ አላበድኩም!

ናታን ኤርሚያስ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19