እናት የኛ ጀግና! አመት ሚፈነጨው : ክብርሽን ሚያጎድል ደርሶ ዛሬ አክባሪ : እናቴ እናቴ ቢል ፤ እሱንም ችለሻል : ይህ አኮ ነሽ አንቺ ማን ብቁ ነኝ ይላል : ሊነጻጸር ከአንቺ ! ብጨነቅ ብጠበብ : ብብሰለሰል ከቶ ስላንቺ ለመጻፍ : ቃላትስ መች በቅቶ! አንቺ አትደረሺም : ጥልቅ ነሽ ከውቅያኖስ ስምሽም በቂ ነው : ውስጥን ልብን ሚደርስ! እናትዬ ስልሽ : የሚሰማኝ ሰላም ወዬ ልጂ ስትዪ : በድምጽሽ ስታከም ፤ ትበልጫለሽ ከሁሉ : ሀኪምም ነሽ ጠጋኝ አንደበትሽ ጠል ነው : ክንድሽ አስተማማኝ። ሁሉን ተሸካሚ : ቻይ አርጎ ፈጥሮሻል እማ አንድ ቀን ሳይሆን : ሁሉም ይገባሻል። ጉድለቶችሽ ሞልተው : ያሰብሽው እየቀና ደስ እያለሽ ኑሪ : እናት የኛ ጀግና!! በሀሴት ዮሐንስ 30/08/2014 ፍቅራችን ለዛሬ ብቻ አይሁን! የእናትን ክፉ አያሰማን! ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት! @bewketuseyoum19 @bewketuseyoum19 9.7K viewsAbela, 15:29