🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

ኢላማህ ............ ቅድሚያ ኢላማው ፡ውስጥ ሰዶ ቀስቱን ለማስገባት፤ ሊሰድ የቆመው ሰ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ኢላማህ
............



ቅድሚያ ኢላማው ፡ውስጥ ሰዶ
ቀስቱን ለማስገባት፤
ሊሰድ የቆመው ሰው፡ አይምሮና እጁ፡
መስማማት አለበት።


ቢሰድ ቢወረውር ፡ኢላማውን ባይመታ ፡
የተወረወረው ቀስት፤
ሁለት ነገር አለ፡ ግቡን እንዳይጨብጥ ፡
የጋረጠው አለት።



አንድ

በድል አጠናቆ ፡ከልቡ ተነስቶ፡
ኢላማውን ለመምታት፤
የወርዋሪው አይን ፡ኢላማው ላይ ብቻ፡
ማተኮር አለበት።

ሁለት

ያየውን ራዕይ፡ እውን ሆኖ እንዲያይ ፡
ግቡን እንዲመታው፤
መስደድ ብቻም ሳይሆን ፡እስከመጨረሻው፡
ቀስቱን ይለጥጠው።




ታዲያ ዋ

ድል ማድረግ ስትፈልግ ፡መንሳፈፍ እንድትችል
ከሰፊው ደመና፤
ለግብህ ትይዩ ፡የሚገኝ ስፋራ ላይ፡
መገኘትህን አጥና።።

ከዚን

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19