🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

እግዜር ላንቺ እድል ትላልቅ ዓይኖችሽ ኮብለል ኮብለል ስሉ እኚያ ውብ ከንፈሮች ከፈት ከደን ሲሉ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እግዜር ላንቺ እድል

ትላልቅ ዓይኖችሽ ኮብለል ኮብለል ስሉ
እኚያ ውብ ከንፈሮች ከፈት ከደን ሲሉ
ከጉንጭሽ ላይ ያሉት እኚያ ስርጉዶችሽ እንዲው ሲዋልሉ
የተመልካችን ልብ ብሎን ያላላሉ
ዘንካታው ፀጉርሽ ደርሶ ሲዘናፈል
እንደ ጦር የቆመው ጡትሽ ሲንከባለል
የቀጠነው ገላሽ በእይታ ላይ ሲውል
ያቃጭላል ከውስጥ የወንድነት ደውል
ከጀርባሽ ላይ ኮርቶ የተፈናጠጠው
ያላፊ አግዳሚውን አንገት የሚያሳጣው
ስሜትን ወጥሮ አካልን ሚያግለው
ስለ ውብ ቁመናሽ ዳሌሽ ምስክር ነው
ቁመናሽ ማማሩ መልክሽ መሽቀርቀሩ
ፀባይሽ የሰጠ ያየለ ቀመሩ
አንቺን እንዳየሁሽ ወደ አምላክ አንጋጠጥኩ
በተሰጠሽ ውበት እጅግ እየታወኩ
ይህን የመሰለ ውበት ባንቺ ፈላ
ከፍጥረታት ሁሉ እግዜር ላንቺ አይላ።


አክሊሉ ተስፋዬ

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19