🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

​​አሁን ስሜቴ ተደበላልቆብኛል ግን አንድ ነገር አውቃለሁ እናንተ ለኔም ሆነ ለሚ ስኪኑ የኢትዮጵያ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

​​አሁን ስሜቴ ተደበላልቆብኛል ግን አንድ ነገር አውቃለሁ እናንተ ለኔም ሆነ ለሚ ስኪኑ የኢትዮጵያ ህዝብ ጀግኖቻችን ናችሁ። በሁሉም ኢትዮጵያዊ ልብ ውስጥ ትኖራላችሁ እቺን ሀገር ሊያፈራርሷት ከተነሡ የቀን ጅቦች ታድጋችሁዋታል....
ኢትዮጵያችን ሀይልና ስልጣን ያላቸው ሠዎች ችግረኛውንና ሚስኪኑን ህዝብ እንደፈለጉ የሚገሉበት፤ የሚያሠቃዪበትና የሚዘውሩበት ሀገር መሆን የለባትም ......
ሁሉም ወንጀለ ኛ በፍትህ ሊዳኝ ይገባል.....አዎ መኩሪያው ምንም እንኳን አባቴ ቢሆንም እሥር ቤት እንዲበሠብሥ እፈልጋለሁ....ለእያንዳንዱ አረመኔያዊ ድርጊቱ ቅጣት እንዲያገኝ ከኔ በላይ የሚፈልግ የለም....
ሚኪ፤ሂዊና ሮቤል አይኔን ስለገለጻችሁልኝ ሳመሠግናችሁ እኖራለሁ..." ሠላም ንግግሯን ጨርሳ በረዥሙ ኡፍፍፍፍፍፍፍፍ ብላ ተነፈሰች....
ሚኪ ሮቤልንና ሂዊን በየተራ አቀፋቸውና ተመልሶ ፍቅሩን ወገቧን ያዝ አደረጋና ባለበት ቆመ።....
ሂዊ እጅግ ደሥተኛ ከመሆኗ የተነሳ ስሜታዊ ሆናለች....ሮቤል ላይ ዘላ ተጠመጠመችበትና ጉንጩን ሳመችው....
ሚኪና ሠላም ሁኔታቸውን አዩና ተጠቃቅሠው ፈገግ አሉ።...

በአንድ ሳምንት ውስጥ ብዙ ነገር ተካሂዷል ወንጀለኞቹ ባለሥልጣኖች ካሉበት እየተለቀሙ በቁጥጥር ሥር ውለዋል....ሁለቱ የወንጀል መናሀሪያ የሆኑት ድርጅቶች በመንግሥት እገዳ ስር ሲሆኑ ከወንጀል ነጻ የሆኑትን ሆቴሎች ሚኪ በይፋ የራሱ አድርጓቸዋል በየክፍለ ሀገሩ ያሉትም የሆቴሎቹ ስሞች በአባቱ ስም እንዲሠየሙ አድርጓል ይሄን ስላችሁ ግን ሚኪ ራስ ወዳድ ሆኖ ድርጅቱን ለራሱ አደረገው እያልኳችሁ አይደለም...
የድርጅቱን የአክስዩን ድርሻ ለአራት ከፍሎታል 40%ቱን የአባቱን ድርሻ እራሱ ሲወስድ 30%ቱን ለሠላም እንዲሁም ቀሪውን 30% ደግሞ ለሂዊና ለሮቤል ሠጥቷቸዋል...
እለተ እሮብ ከጠዋቱ 3:30 ገደማ ሚኪ የቢሮ ስራውን እየከወነ ሳለ ካለምንም መንኳኳት ድንገት የቢሮው በራፍ ተከፈተ....
ሚኪ ካቀረቀረበት ቀና ብሎ ሲመለከት በስካርፕ፤ በመነጸርና በኮፍያ ተሸፋፍኖ ማንነቱ የማይለይ ሠው እየቀረበው ነው.....
ሚኪ ሁኔታው ስላላማረው ጥበቃዎች ለመጥራት እጁን ወደ ስልኩ ሲሰድ...
"እጅህን ብትሠበሥበው ይሻልሀል" አለው የተከናነበው ሠውዬ....
ወዲያውም ኮፍያውንና ስካርፑን በማወላለቅ ለእይታ ተጋለጠለት....
የሚኪ አይኖችና በፓሊስ እየተፈለገ ያለው የመኩሪያው አይኖች ፊት ለፊት ተጋጩ።

ይቀጥላል
Share Share Share
ከወደዱት ሼር ያድርጉ
@bewketuseyoum19