🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

በቀልና ፍንጥርጣሪው ክፍል 41 የመጨረሻ ክፍል ፀሃፊ ሸረፈዲን የእናቱ ልጅ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

በቀልና ፍንጥርጣሪው
ክፍል 41
የመጨረሻ ክፍል
ፀሃፊ ሸረፈዲን የእናቱ ልጅ
.
.
.
ሚኪ መኩሪያውን ሲያየው አየር ላይ ተንሳፎ ተስፈነጠረና አነቀው....
"አንተንማ አልገልህም ካጋሮችህ ጋር እሥር ቤት ፍርፋሪ እንድትበላ ነው የማረግህ" አለና በአንድ እጁ እንደያዘው ስልኩን አወጣ.....
"ተረጋጋ ጩጬው የምታደርገው ነገር ይቆጭሃል" መኩሪያው በሙሉ መኩራራት ነበር የሚናገረው....
"አሁንኮ አልቆልሃል...የምታምንባቸው ሠዎች ሁሉ ወህኒ ወርደዋል....ቤተሠቤን ላደረከው ነገር እድሜ ልክህን ትከፍላለህ"
"ጩጬው በህይወት እሥካለህ ድረስ አለቀ የሚባል ነገር የለም...እንዲያውም ካልክ ፊልማችን ገና ጀመረ....ስማ ወጣቱ እናትህ እኔ ጋር ናት" አለው መኩሪያው
ሚኪ ሠውነቱ ፍም መሰለ....ጡንቻዎቹ ተወጣጠሩ....የንዴቱ ልክ ጥርሱን እስከማንገጫገጭ ደረሰ
"አንተ ውሻ.....ምናባህ ነው ያልከው....? እናቴ የት ነች..? ሚኪ ከግድግዳ ጋር ገፍትሮ አጋጨው..
መኩሪያው በርሊን ሆኖ ሳለ ነው እየተካሄደ ያለውን ነገር ጆሮ ጠቢው ደውሎ የነገረው......ባለስልጣኖቹ እንደታሰሩና የሆቴሎቹ ስሞች አባተ በሚል መጠሪያ እንደተቀየሩ ሲሰማ ነው የድሮው ትዝታው ብልጭ ያለበት......የሚኪን ማንነት ከተገነዘበ በሁዋላ ወዲያው ከጀርመን ተመለሰና ከህግ አካላት እራሱን እየሸሸገ ወደ ጅማ አመራ....ከዛም እናቱን ጠልፎ በሚኪ ደካማ ጎን መጣበት...
"አንተ ልጅ ተረጋጋ እንጂ....እኔን ብትገለኝ ወይም ለፓሊስ ብታሥረክበኝ የእናትህን እሥትንፋስ ለማቋረጥ ሠከንዶችን የማይጠብቅ ታማኝ ሠው አለኝ" አለው መኩሪያው እየሳቀና ከወደቀበት እየተነሳ....
ሚኪ እራሱን አረጋጋ... መኩሪያው ፊት ላይ ለማረፍ የተወጣጠሩት ጡንቻዎቹም ረገብ አሉ.....ቆሞ ግንባሩን ማሸት ጀመረ...
"ሥንት የለፋሁለትን ሀብት በቀላሉ ሠጥቼህ እዛው የምቀር መስሎህ ነበር....ካካካ" መኩሪያው በድጋሜ ሳቀበት
"አንተ ቆሻሻ ሽማግሌ ንብረቱ የአባቴ ነው..." አለው ሚኪ
"ነበር ግን አሁን የኔ ነው....ይልቅ እናትህን ለማትረፍ የምልህን አድርግ.......ሙሉ ሀብቱን ትመልስልኛለህ........ ቦታውን ቴክስት አደርግልሃለሁ..ከአንድ ሰአት በሁዋላ ብቻህን መጥተህ እናትህን አድናት እሷ ብቻ ናት የቀረችህ ቤተሰብ" ብሎት ፊቱን መልሶ ሸፋፈነና ጎምለል ጎምለል እያለ ቢሮውን ለቆለት ወጣ...

ሰላምና ሂዊ ማራማዊትን በመኪና እያንሸራሸሯት ነው..... አሪፍ የሚባል ጊዜ እያሳለፉም ነው.....ህጻን ማራማዊት አይታ የማታውቀውን አለም አንድ ባንድ በግርምትና በመደነቅ ታያለች....በጣም እንደተደሠተች በየደቂቃው የምትሥቀው ሳቋ ይናገራል።.......
የሂዊ ስልክ በድንገት ጮኸ.......በቶሎ አነሳችው...
"ሄሎ ሚኪ"
"ሂዊ መኩሪያው እናቴን አግቷታል.....ምን ማድረግ እንዳለብኝ አላውቅም...አሁን እንድመጣ በነገረኝ መሠረት ወደ ቦታው እየሄድኩ ነው።..."
"ምን ..? ቦታው የት ነው.....?" ሂዊ አመዷ ቡን አለ...
"ወደ አዳማ የሚሄደውን መሥመር ይዘህ ሥትመጣ በጅምር ላይ የሚገኝ ፋብሪካ አለ....እዛ እንድገኝ ነው የነገረኝ....ቻው በቃ መፍጠን አለብኝ" ሚኪ ስልኩን ጆሯዋ ላይ ዘጋባት...
"ምንድነው ሂዊ.....ምን ተፈጥሮ ነው......?" ሠላም ጠየቀቻት
"አባትሽ የሚኪን እናት ይዟታል...እናም ሚኪ ወደ ቦታው እየሄደ ነው"
ሠላም በድንጋጤ መኪናውን ሲጢጥ አድርጋ አቆመችው
"ምን ጉድ ነው ሂዊ...መኩሪያውኮ መመለሻው ቀን አልደረሠም..." አለች ሠላም
"አዎ እኔም ምንም አልገባኝም" ሂዊ ተናገረች
"የት ነው ቦታው....?"
"ወደ አዳማ መውጫው ነው ያለኝ"
ሠላም ወደዛው መኪናዋን በፍጥነት ነዳችው.....
ሂዊ ለሮቤል ደውላ አሳወቀችው.....
"በሰአትህ መጣህ ጩጬው....እያት እናትህን" አለና የተሸፈነውን ፊቷን ገለጠው. ..
"ልጄ.......እዮቤ" አለች እናቱ ወ/ሮ የሺወርቅ እየተንሰፈሰፈች...
"መኩሪያው ይበቃሃል እናቴን ልቀቃት....ይብቃህ" አለው ጮኽ ብሎ
"ባለህበት ተረጋግተህ ቁም ጩጬው...አጉል ጀግና ለመሆን አትሞክር አለበለዚያ የእናትህን አናቷን ነው የማፈራርሠው" አለው ሽጉጡን ወ/ሮ የሽወርቅ ጭንቅላት ላይ እየደገነ
"ተው እንዳታደርገው መኩሪያው" አለው ሚኪ
"ሂድና ፈትሽው..." መኩሪያው አብሮት ላለው ሠው ትእዛዝ ቢጤ ሠጠው...
ሠውዬው አብጠርጥሮ ፈተሸው "አለቃ ምንም አልያዘም" በማለት አሣወቀው....
"እሺ ልጅ እዮብ ያልኩህን ይዘህ መጥተሃል....?"
"ይሄው ግን እናቴን ሳትለቃት አታገኛትም"
ሚኪ የያዘውን ወረቀት ከጃኬቱ ውስጥ አወጣና ወደ ላይ ከፍ አርጎ አሳየው......
"ምንም አማራጭ የለህም....ለሰውዬው ስጠው የያዝከውን" አለ መኩሪያው....
ምንም ማድረግ ያልቻለው ሚኪ ፋይሉን ለሠውዬው አሥረከበ....
"የፈለከውን አግኝተሀል....እሺ አሁን ልቀቃት".....
መኩሪያው ወረቀቱ ላይ የሰፈረው ልክ መሆኑን ካጤነ በሁዋላ ሚኪ ላይ ሽጉጡን አነጣጠረበት...
"እባክህ ተው መኩሪያው ልጄን አትግደለው....ያለኝ እሡ ብቻ ነው.." ወ/ሮ የሺወርቅ እያለቀሠች ለመነችው...
"አይሆንም ይሄ ቤተሠብ እሥካለ ድረሥ ሠላሜን አላገኝም......እንደጀመርኩት እጨርሰዋለሁ....ልጅ እዮብ ገና ድሮ ነበር አንተን መግደል የነበረብኝ" አለና የሽጉጡን መጠበቂያ እንደከፈተው....
"መኩሪያው ተው እንዳታደርገው" ሠላም እየለፈለፈችና እየጮኸች ሚኪን በሠውነቷ ከልላ ጥልቅ አለች....
"ሠላሜ እዚህ ምን ትሠሪያለሽ...ዘወር በይ አሁን ይሄ ባለጌ አምኜ ቤቴ ባስገባውና አንድ ማድ ባቀርበው እጄን ነከሰኝ..ሙሉ ሀብቴን በራሡ ሥም አዞረው" አላት መኩሪያው ሽጉጡን ሳያወርድ.....
"መኩሪያው የሠራሃውን ሁሉ ሀጢያት አውቂያለሁ...አንተ በሰው አምሳል የተሠራህ ዲያቢሎስ ነህ.....ትንሽ እንኳን እንጥፍጣፊ እዝነት የሌለህ አውሬ ነህ....አሁን አንተ ለሠራኸው ሁሉ ክፋት የምትከፍልበት ጊዜ ነው እንጂ ሌላ ወንጀል የምትሠራበት አይደለም። ካንተ በመፈጠሬ እኔም እርኩስ እንደሆንኩ ነው የሚሠማኝ" ሠላም ንዴቷ አየለ...
"ልጄ እኔ ምንም አልሠራሁም...ይሄ ውሻ ነው አይደል መጥፎ ሃሳብ አእምሮሽ ውስጥ የከተተብሽ ልጄ ዘወር በይልኝ...እደፋሃለሁ አንተ ጥላ ቢስ".....
"ልጄ አትበለኝ ልጅህን ገለህ ቀብረሃታል...እነሡን ከመግደልህ በፊት እኔን አሥቀድመኝ....በላ ይሄው ተኩስ" አላችው ሠላም እጇን እየዘረጋች....
"አንድ ቀን እንኳን በምታደርገው ነገር ጸጸት ተሰምቶህ አያውቅም....? አቶ መኩሪያው" የሂዊ ድምጽ ነበር የተሠማው ከነልጇ እነ ሠላምን እየተቀላቀለቻቸው....
መኩሪያው ኩምሽሽ አለ....በፊት መንገድ ላይ የጣላትን ሂዊን ሲያያት ተረበሸ።......የእሷ እዚህ መገኘት ግራ አጋባው.....
"አንቺ ደግሞ እዚህ እንዴት መጣሽ....እሥከዛሬሥ የት ነበርሽ.....?" አለ መኩሪያው በድንጋጤ ልጁ ሠላም እየሠማችው መሆኑን በመዘንጋት...
"ጥሩ የማስታወሥ ችሎታ አለህ.....ከነዚያ ሁሉ ሴቶች መሀል እኔን ማስታወስ በመቻልህ ተገርሚያለሁ.....አየሃት እቺ የአንተ ዘር ፍሬ ናት....የአንተ ደም ባትሆን ከኔ በላይ ደሥተኛ አይኖርም ነበር ግን ደግሞ እሷን በማግኘቴ እሥካሁን ልኖር ችያለሁ" አለችው ሂዊ በግራ እጇ የያዘቻትን ማራማዊትን ፈገግ ብላ እያየቻት....
መኩሪያው ትልቅ መአት ወረደበት.....የራስ ቅሉ የራሱ እንዳልሆነ ሁሉ ከበደው.....
አፍታም ሳይቆይ