Get Mystery Box with random crypto!

ለወንጀለኞች ሽብርንና ፍርሃት በአካላቸው ላይ የምትነዛው ለንጹሀኖች ደግሞ አሸናፊነትንና ድልን የም | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ለወንጀለኞች ሽብርንና ፍርሃት በአካላቸው ላይ የምትነዛው ለንጹሀኖች ደግሞ አሸናፊነትንና ድልን የምታበስረው የፓሊስ መኪና ድምጽ ዊ...ዊ...ዊ...እያለች ከሩቁ ተሰማች.. አከባቢውንም አርበደበደችው።....
"መኩሪያው አብቅቷል.....ወዳጆችህ አራት መአዘን በሆነችው ጠባብ ጨለማ ክፍል እየጠበቁህ ነው.....ነገ ደግሞ እሥከዛሬ ሥትሠሩት የነበረውን ስውር ደባ ሁሉም ሠው በሚዲያ ያየዋል......ዶክመንተሪ ፊልም ተሠርቶልሃል እንኳን ደሥ አለህ " አለው ሮቤል እያፌዘ...
መኩሪያው የህይወት ሩጫው እዚህ ጋር እንዳበቃ ተረዳ...."በነገስኩበት ምድርማ ተዋርጄና የሠው መጠቋቆሚያ ሁኜ ወህኒ አልወርድም"...መኩሪያው በውሥጡ አወራ..
እጁ በካቴና ታስሮ ከፍርድ ቤት ሲወጣ ሰዎች ሲዘልፉትና ሲሰድቡት ብልጭ ብሎ ታየው....
በግራ እጁ የያዛትን ወ/ሮ የሺወርቅን ወደጎን ገፋ አድርጎ ወረወራትና "ማንም ሠው እንዳይጠጋኝ" እያለ የሽጉጡን አፈሙዝ አፉ ውስጥ ከተተው።...
ሁሉንም ነገር ያጣውና የመኖር ተሥፋው የጨለመበት መኩሪያው በሥተመጨረሻ እራሡን ለማጥፋት ቁርጥ ውሳኔ ላይ ደረሰ።
"ተው እንዳታደርገው......የፈጸምከውን እንደዚሁ እረስተህ ከፍትህ ልታመልጥ አትችልም" አለው ሮቤል....
ወዲያውኑ ጥይት ተተኮሰና መኩሪያው ዘፍ ብሎ ወደቀ...
ሁሉም እየሮጡ ቀርበው ሲያዩት መኩሪያው ጉሮሮው ላይ አልተተኮሰበትም.....ጥይቱ ያረፈው ከበስተጀርባ በኩል ትካሻው አከባቢ ነው።...
"አንተ ጨካኝ ሞት ላንተ ትልቅ እረፍት ነው.....እራሥህን እንድታጠፋ አልፈቅድልህም" የሚል የሴት ድምጽ ሠሙ.....ሁሉም ደንግጠው አንገታቸውን ቀና ሲያደርጒ የሠላም እናት ወ/ሮ ምእራፍ ሽጉጡን ሳታወርድ በቅርብ እርቀት ቆማለች።......ሠላም እናቷን በእግሯ ቆማ ስታያት ድንዛዜ ውስጥ ገባች....
ሚኪ እየሮጠ ሄዶ ከሠላም እናት ላይ ሽጉጡን ተቀበለና የእጃቸውን አሻራ በልብሱ እየጠራረገ ለማጥፋት ሞከረ...ሠው የማይደርሥበት ቦታም ደበቀው።..
ሠላም ይሄንን ለማድረግ ንቃተ ህሊና ውስጥ አይደለችም....
የሠላም እናት መናገርም ሆነ መራመድ የቻለችው የሠላም እገታ የተካሄደበት ምሽት ነበር....የሠራተኛዋን ማክዳ ጩኸት የሠማችው ወ/ሮ ምእራፍ ደንግጣ ትነሳና በመስኮቷ ለማየት ትሞክራለች.....ልጇን ሠላም እያንዘፋዘፉ ተሸክመው ሲወጡ ስታይ የማታውቀው ሀይል "ልጄን" ብላ እንድትጮህ አደረጋት...ልጇን ለማዳንም በደመነፍሥ እሥከ ክፍሏ በራፍ ተራመደች...ወ/ሮ ምእራፍ ግን መራመዷንም ሆነ መናገሯን አላስተዋለችም። ከድንጋጤዋ ሥትነቃ እራሷን ከአልጋዋ ላይ በራፉ ጋር አገኘችው
"እንዴ...ይሄ ምንድነው.....?" አለች ድምጽ አውጥታ....
ከዛን ቀን በሁዋላ እንግዲህ ማንም ሳያያት ከአልጋው እሥከበራፉ ያለውን ቦታ በማካለል የሶምሶማ ሩጫ በሚመስል መልኩ መለማመድ ያዘች።...በጥቂት ሳምንታት ውስጥም እንደማንኛውም ሰው መናገርና መራመድ ቻለች........
ለማንም ግን አልተናገረችም ለራሷ ሚስጥር አድርጋው ቆየች....
ልክ እንደ እነ ሚኪ ቡድን ሁሉ እሷም በራሷ መንገድ ፍትህ ለማግኘት መኩሪያው የሚያደርገውን በድብቅ ሥትከታተል ነበር.....እየተካሄደ ያለውን ነገር አብጠርጥራ ታውቃለች.....
መኩሪያው ሚኪን ለማስፈራራት ወደ ቢሮው ከመሄዱ በፊት መኖሪያ ቤቱ ተደብቆ ገብቶ ነበር...ሮቤልን የት እንደሚቀጥሩት ከጓደኛው ጋር ሲያወራ ነበር.....ያኔ ነው እንግዲህ ወ/ሮ ምእራፍ መኩሪያውን ቦታው ድረስ ተከትላው አሁን ልትተኩስበት የቻለችው......
"እማ እያየሁት ያለሁት አንቺን ነው...? እውነት ድምጽ አውጥተሽ የተናገርሽውሥ አንቺ ነሽ.....?" ሠላም እያለቀሠች ጠየቀቻት....
"አዎ እኔ ነኝ የኔ ልጅ....
ነይ እቀፊኝ" ወ/ሮ ምእራፍ ልጇን ለማቀፍ እጇን አሠፋች..ሠላምም ሌላ ጥያቄ ሳታስከትል እጉያዋ ገባች።......
በጥቂት ደቂቃዎች ውስጥ ሮቤል ይዟቸው የመጡት ፓሊሶች አከባቢውን ወረሩት...መኩሪያውን ይዘው ወደ ሆስፒታል ሄዱ።....
አዎ መኩሪያው ከጥይቱ ሊተርፍ ችሏል ከእሥር ቤት ግን በምንም ተአምር ሊድን አይችልም።
የፍርድ ሂደቱ ተጀምሮ የመኩሪያው አጋሮች እያንዳንዳቸው 22 አመት ሲፈረድባቸው መኩሪያው ግን በአምስት አይነት ውንጀላ ክስ ተመስርቶበት ማለትም በህገወጥ ንግድ፤ በህገወጥ የገንዘብ ዝውውር፤ በአሥገድዶ ደፈራ፤በግብር ማጭበርበር ውንጀላና በነፍስ ግድያ ወንጀል የእድሜ ልክ እሥራት ተፈርዶበት ወህኒ ተወረወረ።......መኩሪያውና ባለስልጣኖቹ የአንድ ሰሞን የቡና መጠጫ ወሬ ሆኑ.....ያሞገሣቸውና ወደ ላይ ከፍ ያደረጋቸው ህዝብ መልሶ አወረዳቸው....መልሶ አወገዛቸው።...