Get Mystery Box with random crypto!

መኩሪያው ከተፈረደበት ከ7 ወር በሁዋላ አራቱ የእውነት ታጋዮች አዲስ ድርጅት ሊያስመርቁ ሽር ጉድ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

መኩሪያው ከተፈረደበት ከ7 ወር በሁዋላ አራቱ የእውነት ታጋዮች አዲስ ድርጅት ሊያስመርቁ ሽር ጉድ ላይ ናቸው.....
ህንጻው በሰዎች ተሞልቷል....
ጎዳና ላይ የወደቁ ልጆችንና በሴት አዳሪነት የሚተዳዳሩ እንሥቶችን አቅፎ የተሻለ እድልና ሥራ ለመፍጠር የተቋቋመው ድርጅት ሊከፈትና ሥራ ሊጀምር ደቂቃዎች ቀርተውታል....
ድርጅቱ የተሠየመው በሂዊ ስም ሲሆን የበላይ አሥተዳዳሪዋም እራሷ ሂዊ ናት..........
ሂዊ ከሌላው ቀን በተለየ ሁኔታ አምራና ደምቃ የመክፈቻ ንግግር ለማድረግ ወደ መድረክ ወጣች።....
"ክቡራንና ክቡራት....ጊዚያችሁን ሠውታችሁ እኛን ለማገዝና ለመደገፍ እዚህ ድረሥ የመጣችሁ ወንድሞቼ፤ እናቶቼ፤እህቶቼና አባቶቼ ለትብብራችሁ ምስጋናዬን በድርጅቱ ሥም አደርሳለሁ።...
ለዚህ እንድበቃ ከእግዛብሄር ቀጥሎ ብዙ ሠዎች ሚናቸውን ተጫውተዋል ይሄን ቀን ለማየት ባያድላትም እናቴ የመጀመሪያዋ ናት...እንደ እናቴ ተንከባክበው ያቆዩኝ እትዬ በለጡ፤ወንድሜ እዮብና ጓደኞቼ ሮቤልና ሠላም አሁን ፊት ለፊታችሁ የቆመችውን ህይወትን ሠርተዋታል.. ምስጋናዬ ጥግ ድረስ ነው እናንተ በህይወቴ ውስጥ ባትኖሩ ዛሬን አምራ አላያትም ነበር።
ከዚህ በመቀጠል አጠር አድርጌ አንዳንድ ነገሮች ለማለት እሞክራለሁ።....
ድርጅታችን በሀሳብ ደረጃ እንጂ በተግባር ያልተገባባቸውን ሥራዎች ለመስራት ቆርጦ ተነስቷል።........አንግበን የተነሳንበት አላማ አንድና አንድ ብቻ ነው....እንደዘበት የሚጠፉትና የሚበላሹትን ሀይ ባይ ዘመድ የሌላቸውን ወንድሞቻችንና እህቶቻችንን አዲስ ህይወት መሥጠት ነው....
ልንገፋቸው አይገባም...ያሉበትን ሁኔታ እያየን መንገዳችንን መቀጠል የለብንም...ዘወር ብለን ልናያቸው፤ልንደግፋቸውና ልንረዳቸው ይገባል......
ማንም ሠው ፈልጎ ጎዳና ላይ እራሱን አይጥልም ማንኛዋም ሴት ፈልጋ ሴተኛ አዳሪ አትሆንም ህይወት ናት አንድ ቀን በማእበሏ ገፍታ ውጥንቅጡ የወጣ ኑሮ ውስጥ የጨመረቻቸው።......
ባትዛመጂውም/ባትዛመደውም መንገድ ላይ ብርድና ጸሀይ የሚፈራረቅበት ኢትዮጵያዊ ነው....የተለያየ ቋንቋ፤የተለያየ ባህል፤የተለያየ እምነት ያለን ህዝቦች ነን ነገር ግን አንድ ደም አለን። እሡም ኢትዮጵያዊ..
...እኛ ኢትዮጵያዊ ነን ስለዚህ ልናዝንላቸውና እጃችንን ልንዘረጋላቸው ይገባል..... ከደገፍናቸው ከተለያዩ ሱሶች ወጥተው ዶክተር፤መሀንዲስ፤የሀገር መሪና ሌላም ሌላም ይወጣቸዋልና ሁላችንም ተረባርበን ለውጤት እናብቃቸው.....
የተለያዩ ድርጅቶችም ሆነ ግለሰቦች በሀሳብ፤በጉልበት፤በእውቀትና በገንዘብ እንድትደግፉን ስል እጠይቃለሁ። አመሠግናለሁ" ሂዊ ንግግሯን ካደረገች በሁዋላ በከፍተኛ ድጋፍ ከመድረክ ላይ ወረደች........
ዝግጅቱ በጥሩ ሁኔታ መካሄዱን ቀጥሏል......ሚኪና ሰላምም ቆመው ሻምፓኝ በብርጭቋቸው እየጠጡ ነው.....
ሂዊ በተናገረችው ነገር ውስጡ አለቅጥ የረካው ሚኪ ያሉበት እሥክትመጣ አልታገሠም...እሷ ጋር ለመድረስ ጥቂት ተራመዳና አሞካሻት.....ሲመለስ ግን ሰላም በቦታው የለችም።..."ሠላሜ" በማለት እየተጣራ ቢፈልጋትም አጣት። መታጠቢያ ቤት ሄዳ ይሆናል በሚል ግምቱ ሊፍልጋት ወደዛው ጎራ አለ...."ሠላሜ እዚህ ነሽ" ሚኪ መጸዳጃ ቤቶቹን በየተራ ያንኳኳል ነገር ግን ያላሰበው ነገር ገጠመው.....
በዛ ያሉ ሰዎች እንዳይላወሥ አድርገው ያዙትና ፊቱን በጨርቅ ሸፍነው ይዘውት ሄዱ...
ሚኪ ማንነታቸውን ለመለየት እንኳን ጊዜ አላገኘም ሁሉም ነገር በፍጥነት ነው የሆነበት።.....
"እነማን ናችሁ....? ልቀቁኝ" እያለ ይለፍፋል...
ሠዎቹ በብርሃን የተሞላ ክፍል ወሠዱትና ፊቱን የሸፈኑበትን ጨርቅ አነሡለት..
"ምንድነው ምትፈልጉት....?" ሚኪ አይኑን አጨንቁሮ አከባቢውን እያማተረ መቃኘት ጀመረ...
በብርሃን ጨረሩ የተንሸዋረረው አይኑ ሰርፕራይዝ ሆነ ድምቅ ያለ አብረቅራቂ ነጭ ሱፍ ፊት ለፊቱ ተሠቅሏል።
"ሠርፕራይዝ ጓደኛዬ"....ሮቤል እየሳቀና እያጨበጨበ ወደ ክፍሉ ገባ .....
"ሮቢ....አንተ ነህ ይሄን ሁሉ ያደረከው ..?"
"አዎ እኛ ነን...አሁን ቶሎ ልበስና ተዘጋጅ ዛሬ ልታገባ ነው.....ሠርጋችሁ የማይረሳ ነው የሚሆነው"
"አንተ የምትገርም ፌዘኛ ሰው...እሺ ሠላሜስ...?" ሚኪ ጠየቀ
"እሷንም እንዳንተው ሴቶቹ ሰርፕራይዝ አድርገዋታል...ሃሃሃሃ"
"ሮቢ ሠላሜን እንደኔው አስጨንቃችሁዋት ከሆነ ገደልኳችሁ...ሃሃሃሃ"....
ሚኪ ከ30 ደቂቃ በሁዋላ በሙሽራ ቬሎ የደመቀችውንና እጅግ የተዋበችውን ሠላምን ይዞ በህዝብ ፊት ወጣ....
ታዳሚው በጩኸት ቤቱን አደበላለቀው.....ታዳሚው እራሱ ያልጠበቀው ሠርፕራይዝ ሆኖበታል...
ሙሽሮቹ ቃለ መሀላ ፈጸሙና በይፋ ባልና ሚስት ሆኑ።...
ሚኪ እጇን ያዘና ግንባሯን ሳም አደረጋት .....
"ቆይ ባሁኑ ህይወታችን ማን ብዬ ነው የምጠራህ.....ሚኪ ወይሥ እዮብ....?" አለችው "
"እዮብ ይሻለኛል....ውሸታሙ ሚኪ ምን ያደርግልሻል" አላትና እሡም በተራው ሳቀ....
ሠላም የእዮብን(የሚኪን) እጅ ሆዷ ላይ አሥቀመጠችው "እዮቤ(ሚኪ) ልጅ ሊኖረን ነው......የ3 ወር ቅሪት ነኝ" አለችው እየተፍለቀለቀች
"እውነትሽን ነው ሠላሜ....? እዮብ(ሚኪ) በደሥታ ሰከረ።...
ከንፈሯም ላይ ተለጠፈባት......ታዳሚዎቹ እያዩዋቸው እንደሆነ ዘንግተውታል። ፍቅር አይናቸውን ጋርዷቸዋል..መስሚያቸውን ደፍኖቷል.....አሁን እሷና እሱ ብቻ ናቸው።....
ከነጎዱበትና ከጠለቁበት አለም የመለሳቸው ....ይሄን ፊልም የሚመስል ሠርግ ሲከታተሉ የነበሩት የታዳሚዎቹ የሞራል ጩኸትና ፉጨት ነበር።......
ሮቤል መድረክ ላይ ወጣና ማይኩን በእጁ ጨብጦ "እንኳን ደስ አላችሁ ጓደኞቼ ...ሠርጋችሁን የአብርሃምና ሳራ ያድርግላችሁ..."አላቸው
ቀጣዩን ንግግሩን ለማድረግ ግን ድፍረት አጣ ሮቤል...."እህህህ....እእእ" ማለት ጀመረ....ነገሩ የገባው ሚኪ በአይኑና በእጁ እንዲናገረው አበረታታው...
"ሮቤል ዛሬ ነው እድልህ...አድርገው" ከራሱ ጋር አወራ
"ሂዊ" አለ ሮቤል. .......
"ሂዊ ቃላቶችን ቀምሜ መናገር አልችልም ለፍቅር ገና ጀማሪ ነኝና.."
ብዛት ያላቸው አይኖች ሂዊ ላይ አፈጠጡ ....ሂዊ ውስጧ ቢደሠትም አፍረት ተሠማት.....
ሮቤል ንግግሩን ቀጠለ "ሂዊዬ በጣም አፈቅርሻለሁ ይሄን አንቺም ታውቂያለሽ"....ከኪሱ ቀለበት አወጣና በጉልበቱ ተንበረከከ
"ሂዊዬ አንቺን ካገኘሁ በሁዋላ እየኖርኩ እንደሆነ አወቅኩ...ዛሬ እሺ ብለሽ ብታገቢኝ ከኔ በላይ ደሥተኛ አይኖርም........ለልጅሽ ምርጥ አባት ለመሆንና ከአጠገብሽ ሳልለይ ልጠብቅሽ ቃል እገባለሁ....ሂዊዬ ታገቢኛለሽ.....?"
ሂዊ ድፍረቱን አጥታ እንጂ ሮቤልን ማሠብ ጀምራለች.....ታዳሚውም እሺ እንድትለው ግፊት አደረገባት...
"ሂጂ ልጄ...ሂወትሽን ኑሪያት..ይሄ በህይወትሽ አንዴ የሚመጣ የፈጣሪ ጸጋ ነው....ሂጂ ተደሠቺ" አሏት ከጎኗ የቆሙት እትዬ በለጡ...
ሂዊ ብርክ እየያዛት ልጇን ማራማዊትን አሥከትላ ወደ መድረኩ ወጣች.....
ከተንበረከከበት አነሳችው "እሺ አገባሀለሁ...አድርግልኝ ቀለበቱን" አለችው እየሳቀች..
ሮቤልም ቀለበቱን አጠለቀላትና ሁለቱንም እቅፉ ውስጥ አስገባቸው።....


ከሁለት አመት ከ5 ወር በሁዋላ....