Get Mystery Box with random crypto!

ትልቁ መኖሪያ ቪላ ምግብ ምግብ ይሸታል.......ቤተሠብ ተሰብስቧል...ሚኪ(እዮብ) ፣ ሠላም፣ ሂዊ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ትልቁ መኖሪያ ቪላ ምግብ ምግብ ይሸታል.......ቤተሠብ ተሰብስቧል...ሚኪ(እዮብ) ፣ ሠላም፣ ሂዊ ፣ ሮቤል ፤ ወ/ሮ የሺወርቅ ፤ ወ/ሮ ምእራፍ፣ እትዬ በለጡ፣ ማክዳ፣ ህጻን ማራማዊትና ሌሎችም የተጋበዙ እንግዶች በአንድ ጣሪያ ስር በህብር እየተደሰቱ ነው.....ምክንያታቸው ደግሞ የእዮብ(ሚኪ) እና ሠላም የአብራካቸው ክፋይ የሆነው ኪሩቤል እዮብ እቺን ምድር ከተቀላቀለ ሁለተኛ አመቱን በመያዙ ነው.....
ሁለቱ የኪሩቤል አያቶች እየተቀማሙ ያቅፉታል ያጫውቱታል ወላጆቹ እዮብ(ሚኪ) እና ሰላም እራሱ ልጃቸውን የማቀፍ መብት የተነጠቁ ይመሥላሉ....
የልደት ስነ ስርአቱ ሊጀመር ሲል አጠገባቸው ያለው ቴሌቭዥን ሠበር ዜና ብሎ አወጀ.....
ሁሉም የሚከተለውን መጠባበቅ ያዙ....
"ሰበር ዜና ታዋቂው የንግዱ ሠውና በሁዋላም በአምስት የወንጀል አይነቶች ፍርድ ተበይኖበት ለእድሜ ልክ እሥራት የተጋለጠው አቶ መኩሪያው ትላንት ሌሊት ባልታወቀ ምክንያት ሞቶ ተገኘ።....ፓሊስ ጉዳዩን እያጣራ ሲሆን እኛን ተጨማሪ መረጃ ስናገኝ የምናቀርብ ይሆናል" አለ በቲቪው ውስጥ የሚታየው ጎልማሳ ጋዜጠኛ....
ሠላም ስጋዋ ስለሆነ ትንሽ ተሰምቷት ትክዝ አለች....ወዲያው ቲቪው ጋር ደርሳ አጠፋችውና ፈገግ ብላ የልደት ዝግጁትን እንጀምር አለቻቸው።....
.
.
መልካም ልደት ለኪሩቤል
.
.
.
.
.
//~~ተፈፀመ//
Share Share Share
ከወደዱት ሼር ያድርጉ
@bewketuseyoum19