Get Mystery Box with random crypto!

የባስሊቆስ ዕንባ ብዙ ያልተዘመረለት ፣ ማህበራዊ ሚድያው ያልጮለኸለት መጽሐፍ ነው። ውድ ነገር | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የባስሊቆስ ዕንባ

ብዙ ያልተዘመረለት ፣ ማህበራዊ ሚድያው ያልጮለኸለት መጽሐፍ ነው። ውድ ነገር በርካሽ ፍራንካ ያገኘሁ ያህል ነው የተሰማኝ። መፅሐፉ በጣም ሚያስገርም መጽሐፍ ነው። በጣም የሚያምር የቋንቋ ለዛ ያለው ፣ አተራረኩ ማይጎረብጥ የጻህፊዋን የላቀ ስነፅሁፍ ችሎታ ሚያሳብቀ ድንቅ መፅሐፍ ነው። ደራሲዋ ትዕግስት ታፈረ ሞላ ትባላለች። ሴት ደራሲዎቻችን ወደፊት ሲወጡና በዚህ ልክ አቅማቸውን ሲያሳዩ ህይወትን እንደ ገብስ ግርዱን ከገላባው ለይተው ያስመለክቱናል ያሰኛል። በእያንዳንዱ ገጽ በሀሳቦቿና በመልዕክቷ አድናቆቴ ቀርቶላታል። ስለ ዕንባችን ፣ ስለ ህመማችን ፣ ሳቃችን ፣ ስለ ሀገራችን ፣ ስለ ፍቅር ሀያልነት ፣ ስለኑሮ ስቃይ በማራኪ መንገድ ከትባልናለች። ሀሳቧ ያምራል ፣ ገለጻዋ ያምራል።

በጣም ያስደሰተኝ ደግሞ መፅሐፏ ወደ ፊልም ተቀይሯል። በ Dstv '' አቦል ቲቪ '' ላይ በተከታታይ ክፍል እየታየ ነው። ያነበቡትን መፅሐፍ በፊልም ሲመለከቱት የእውነት አለም ነው።

እንድታነቡት ተጋብዛችኋል።

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19