Get Mystery Box with random crypto!

ቀድሼ :ላግባሽ.. 2.... የጸሎተ:ሐሙስ:የክርስቶስ:ራት በረከት:የቀመሽ:በፈለግሽው:ሰዓት ል | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ቀድሼ :ላግባሽ.. 2....


የጸሎተ:ሐሙስ:የክርስቶስ:ራት
በረከት:የቀመሽ:በፈለግሽው:ሰዓት
ልሳንሽ:ወለላ:ፊደላትሽ;ስኳር
እንደ:ዮሐንስ:አፈ:ወርቅ:አፈ;ማር:አፈ:ማር !
:
በዻውሎስ:መፅሐፍ:እንደተነገረው
የስጋሽን:መንፈስ;ስሜት:ሳያረክሰው
በመንፈስ ቅዱስ :ኃይል:የከበረውን:ቤት
በወጣትነትሽ:የጠበቅሽ:ክቡር:ሴት

የዘመኑ :ልማድ:የዘመን:ፍካሬ
ያላስገረሰሰው:የህግሽን :ፍሬ
መዐዛው:ያራቀሽ:የክብር:ከልበኔ
ምስጢሩ:የገባሽ:የወንጌሉ:ቅኔ
በግዕዝ:በዕዝል:ስርአት:መልሼ
እባክሽን:ላግባሽ:ራሴው:ቀድሼ!!
ምዕመን:ይጠንቀቅ:ዘንድ:ከዝሙት:ፈተና
አንድ:ሰው:ካንድ:ሰው:ወንጌል;ፈቅዷልና
።።ቃል:ለሰማይ :ብለሽ:እኔም:ቃል ;ለምድር
የአብርሃምን:ህይወት:እባክሽ:እንጀምር!
በጌታ:ተአምር:በስልጣኑ:ቀመር
ፀንቻለሁና:ከእስጢፋኖስ:ማህበር
ነጠላ:ሳትጥዪ:ቀለም:ሳትቀቢ
አይንሽን:ሳይጋርድ:እኩይ:እንደረቢ
ጸዋጋን:ሳይሰልቡን:ጠብቀው:አሳቻ
ጥበብ:እንድስይሸሸን:የእግዚአሔር:ፍራቻ
ላንቾም:ጸጋ:ጽናት:ለኔም:ህይወት:ብርታት
እንዲወረብልን:ትዌድሶ:መርዓት...*...
:
በእዝል:በግእዝ:ስርአት:መልሼ
እባክሽን:ላግባሽ:ራሴው:ቀድሼ!!

Poet :Dawit tumey

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19