Get Mystery Box with random crypto!

ብለሽኝ አልነበር? ብለሽኝ አልነበር? ዝምታህ ነፍሴ ነው ፀጥታህ ያምረኛል በዘጋ አንደበትህ ልብህ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ብለሽኝ አልነበር?

ብለሽኝ አልነበር?
ዝምታህ ነፍሴ ነው ፀጥታህ ያምረኛል
በዘጋ አንደበትህ ልብህ ይሰማኛል
ዝምታህ ነፍሴ ነው
ፀጥ በል ስላልሽኝ ይሄው ዝም አልኩልሽ
ሳስመስል የግዴን
ማውራት እያሰኘኝ አፌን ዘጋሁልሽ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ብለሽኝ አልነበር?
ሳቅህ ገነቴ ነው ፈገግታህ ገዝቶኛል
ሳቅልኝ በሞቴ እኔን ደስ ይለኛል
ሳቅህ ገነቴ ነው ፍካልኝ ስላልሽኝ
ሳስመስል የግዴን
የውሸቴን ሳገጥ ሳሽካካ አስመሸሽኝ
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ብለሽኝ አልነበር?
ድምፅህ ግዛቴ ነው ምቾት ይሰማኛል
'እወድሻለሁ' በለኝ ይሄ ቃል አምሮኛል
ድምፅህ ግዛቴ ነው ደጋግመው ስላልሽኝ
ሳስመስል የግዴን
'እወድሻለሁ' ብል በስምሽ አስማልሽኝ
("ሙች በል እስኪ" እያልሽኝ)
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።

ብለሽኝ አልነበር?
ሀዘንህ ጌጤ ነው ያፍነከንከኛል
አንዴ አንብተህ ልይህ ይሄ ቀን ናፍቆኛል
ሀዘንህ ጌጤ ነው ተሰበር ስላልሽኝ
ሳስመስል የግዴን
ላንባ ብል እንቢ አለ እዚ ላይ ከበድሽኝ

(የምን ማስመሰል ነው የምንድን የግዴን?
ከአንቺ ያገጣጠመኝ
ቀኔን እያስታወስኩ ላንባልሽ የምሬን )
።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።።
ብለሽኝ አልነበር?


በአቤኒ የተፃፈ


ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19