Get Mystery Box with random crypto!

አሸዋው የማን ነው? አለቱስ የእግዜር? ቤት ስሩ ለማለት ምንድን እንዲህ ማሴር? ፨ «...አ | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አሸዋው የማን ነው?
አለቱስ የእግዜር?
ቤት ስሩ ለማለት
ምንድን እንዲህ ማሴር?



«...አለቱ
አይበገር ቢገፋ፣
ላይፈርስ ሚያለፋ፣



«...አሸዋ
እፍፍ ናት፣
ብንን ናት፣
የነፋስ ድል እራት፣
በእርሷ ታዛ ስታድር፣
“መፍረስን ግን ፍራት”!
ታዲያ
ተናናነቀኝ በቀኝ መልስና ጥያቄ፣
ይገለጣል ቢሉኝ፣
መገላለጥ ሆነ፣
ማደሪያዬን ፍቄ!

«...አለት ነኝ
አልነቃነቅም ብል አፌን ሞልቼ፣
ፈራሽ ነኝ ለንፋስ ብል ግፊት ሸሽቼ፣
ነፍሴን ምን ሊጠቅማት?
መኖሯን ነው የቀማት!

ከአለት
ካ'ሸዋ
አልተሰራም ቤቴ..
ከምን?
ለሚሉኝ ግን ለመመለስ ፈራው፣
አሸዋውስ ነበር ከቤቴ የተሰራው!

ናታን ኤርሚያስ

.
@nathanErmias
@nathanErmias

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19