Get Mystery Box with random crypto!

ጓደኛ '''''''''''' የጭንቀቴ ሸክም አላራምድ ብሎ፥ሲያስድኸኝ በዳዴ፤ የኑሮ ውጥረቷ ላይታች | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

ጓደኛ
''''''''''''
የጭንቀቴ ሸክም
አላራምድ ብሎ፥ሲያስድኸኝ በዳዴ፤
የኑሮ ውጥረቷ
ላይታች ጠፍሮ፥አለምድ ሲል ሆዴ፤
"ምን ሆንክ?" በለኝና
ችግሬን አብርረው፥ተው አግዘኝ ጓዴ፤
ጭንቅህ ጭንቄ ይሁን፥መንገድህ መንገዴ!

ከአንድ ሆድ ባናድር
. . . ኖረን በአንድ መንደር፤
በአንድነት ገምደውን
. . . እምነትና ፍቅር፤
ዛሬ እንደ ባይተዋር
ችግሬን ታቅፌ ለምን ብቻ ልቅር?
.
ከየት ተደብቆ?
.
ላንተ መቼ ጠፍቶ
ውስጤን እያነበብክ፥በፊት ገፄ መድረክ፤
ዓይኔን ካየኃቸው
ከሊቅ እስከ ደቂቅ፥የለም የሚደበቅ፤
ክፍተትህን ልሙላ
ከጎኔ ሁንና፥ሸፍን የኔን ስንጥቅ፤
አንተም በኔ ፈንድቅ፤
እኔም በአንተ ልድመቅ..!

ላርም ስህተትህን
. . . የአይምሮህን ፍዳ፤
ጥረገው ሰንኮፌን
. . . ከህይወቴ ሜዳ፤
አይደለሁ የአዞ አልቃሽ
. . . አይደለህ እንግዳ...

ከጥንት ከበፊቱም
የህይወት ቀኖናን፥ከአስተምሮት ጓዳ፤
ንዋይ አሸንፎት
አሳልፎ ባይሰጥ፥ወዳጁን ባይከዳ፤
ከልቡ የመረጠው
ጓደኛው ነበረ፥ለኢየሱስ ይሁዳ!


አብርሃም ፍቅሬ
(የቅዳስ ልጅ)

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19