🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

የሚደንቅ ቸርነት *** ምንም ቢጨክኑ ሰው በመሆን መሐል አይጠፋም በጎነት... ከሰይጣን በከፉ ል | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

የሚደንቅ ቸርነት
***

ምንም ቢጨክኑ
ሰው በመሆን መሐል
አይጠፋም በጎነት...
ከሰይጣን በከፉ
ልቦች እንኳ መሐል
አይጠፋም ቅንነት...
"ሳንገለው እንዳይሞት"
በሚል አዘኔታ
አይሁድ ለክርስቶስ ያኔ እንደራሩለት
ዛሬም በዘመኔ አሉ ሚያስደንቁኝ
በሚደንቅ ቸርነት...

ሳናጠፋው እንዳይጠልቅ
ሳንጥለው እንዳይወድቅ
ብለው የሚከቱ
ከአሳር ከመቀመቅ !

#Dagmawi

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19