🔥 Burn Fat Fast. Discover How! 💪

እንዲሁ ስከተልሽ እውነት እግዜሩን አላውቀው ከደጁ አልቀርበው እንደሰው ሄጄ መሬቱን | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

እንዲሁ ስከተልሽ

እውነት

እግዜሩን አላውቀው
ከደጁ አልቀርበው
እንደሰው ሄጄ መሬቱን አልስመው
ወይ ፀሎት አላደርስ
ቅዳሴ አላስቀድስ
አባቴ ሆይ ማረኝ ብዬ እኔ አላለቅስ
ዳዊቱን ስደግም መች እኔ እገኛለሁ
ማህሌት ሰአታቱን በእንቅልፍ አልፋለሁ
እንዲህ እንዲህ እያልሁ እርሱን ረስቼ
መጠጥ ጭፈራ ቤት ተስቤ ገብቼ
አንድ ቀን አየሁሽ ከቅዱሱ ስፍራ
ነጠላን ጣል አ'ርገሽ ከምዕመናን ጋራ
አምላኬ ተመስገን
በደሌንም ማረኝ ስትይ ሰማሁሽ
ቀልቤን ገዛሽና እንዲሁ ተከተልኩሽ
አንቺ ካለሽበት
በደመነብስ ስቀርብ ራሴን አየሁት
ለእልፍ አእላፍ ዘመን ደርሶ የማያውቀውን
ከእግዜሩ ግቢ እግሬን አገኘሁት

ስብሀት ለአብ ለወልድ ለመንፈስቅዱስ ብዬ ተሳለምኩኝ
አንቺ እንዳደረግሺው
ከበሩ ሰግጄ መሬቱንም ሳምኩኝ
ካጠገብሽ ሆኜ ስብከቱን ሰማሁኝ
ስትወጪውም ከኋላሽ ተከትዬሽ ወጣሁ
ስምሽን ጠይቄ እንደምንም ተግባባሁ
ምስጋና ለፍቅርሽ
ቀና ብዬ አምላክን የ'ኔ አድርጋት አልሁት
ደግሜ ደግሜ ደግሜ ጠየቅሁት
እሱም አልጨከነ እንደኔ አይደለም
ለፀሎት ጥያቄ ምላሽ አልነፈገም
ወድጄሽ ነውና
አንቺን ፍለጋ እግርሽን ስከተል
አትጠፊም እና ቤተ ክርስቲያን ስውል
አጠገብሽ ቆሜ
ውዳሴን ከፍቼ ስቡህኒ ብለው
ዳዊትን ደግሜ
አምላኬ ሆይ ማረኝ ብዬ ብማፀነው
የ'ኔ እንዲያደርግሽ ማህሌቱን ብቆም
ፍቅርን ፍለጋ
ልብሽ አሸፍቶኝ ገዳማቱን ብዞር
በፀሎት በስግደት በፆም ውዬ ባድር
ንስሀ ገብቼ በይቅርታ ወደቅኩ
ከረሳሁት ጌታ በሂደት ተታረቅኩ
ለካ በምክንያት ነው አንቺን ያስወደደኝ
ባ'ንቺ ተማርኬ ከቤቱ እንድገኝ
ልብሽ አሸፍቶኝ እንዲሁ ስከተልሽ
ከተጣላሁት ቤት
ከአባቴ እርስት ዞሬ ገባሁልሽ።

ሰላም ላንተይሁን

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19