Get Mystery Box with random crypto!

አዙሪት ።።።።። አንዳንዴ... እንዲህ አስባለሁ... አይሁድ ክርስቶስን... ባይወጋ ባይገርፈው. | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አዙሪት
።።።።።

አንዳንዴ...
እንዲህ አስባለሁ...
አይሁድ ክርስቶስን...
ባይወጋ ባይገርፈው...
ተለቀሀል ብሎ...
በርባንን ባያልፈው...
አስራ ሁለት ዙር...
ሰንሰል አሰርቶ...
ከገነት ደጃፍ ላይ...
ሚካኤልን ጠርቶ...
በርባንን ጠፍንጎ...
በቸነከረልኝ ምነበር እላለሁ...
ለሞተልኝ መሲህ...
ጥብቅና እቆማለሁ...

------------------------------

ግን'ኮ ማርያምን...
አዙሪት አይደለም...
ጠምቆኝ ብሰክር ነው...
የሰውነት ቀለም...
ማርያም ባታለቅስ...
መስቀሉን ታክካ...
በወጉ በጦምን...
ቀርቶብን ፋሲካ...
እግር ማጠብ ትተን...
እግር ባልቆረጥን...
ወዳጅ መሆን ቢያቅት...
ሰው ስመን ባልሸጥን...

----------------------------

ዘንባባ ባንቀጥፍ...
ለመልካም መካሪ...
መቆለፍ ከበደን...
የአመንዝራን ሱሪ....
ከፈትነው...
ዚፑን ወለል አርገን...
የደቂቃ ግልቢያ ...
ግለቱ በልጦብን ከገነት ወጋገን...
ከንፈር ተዘላዘልን...
ገላ ተቋደስን...
ዳሌ ስንጨመድድ...
የመሲሁን ቅኔ እየደመሰሰሰን
ዘለልን በአልጋው ላይ...
ሾርን በወለሉ...
ፋፋን በእንቡጦች ደም...
ሳጥናኤል ተዝናና
ስራው በመቅለሉ
በርባን ቢሆን ሟቹ...
ወንበዴው ቢደማ...
ይጣፍጠን ይሆን?
ሰው የመሆን ዜማ?
ጨለማው ባይነግስ...
ቀን በቀንነቱ ብርሀን ቢሰፍበት...
የቤተመቅደስ ጨርቅ ቁልቁል ባይመተር ዕድሜ ሰጥቶት ቢቀር
እንዲያ እንዳማረበት...
ለገረፉት ባይጮህ...
ምህረትን ከአባቱ...
ሰው ሰው እንሸት ይሆን?
በበርባን ስቅለቱ?
ደቅሲዎስ ገላውን
ገንዞ ባይቀብረው
የትንሳኤው ዜና
አይሁድን ባይገርመው
በርባን ቢሞት ኖሮ
በክርስቶስ ቦታ
እኔ እነሳ ይሆን
የማታ የማታ?

በማዕዶት ያየህ
(ሀሳቡ ከሌላ የተወሰደ)

13/08/2014 ዓ.ም.

ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19