Get Mystery Box with random crypto!

አንዳንዴያችን የኔ እና እሷ አንዳንዴ ስትሄድ በመንገዷ ስሄድ በመንገዴ ልትፈልገኝ ስትመጣ ልፈል | በእውቀቱ ሥዩም እና ሥነ-ፅሁፍ

አንዳንዴያችን

የኔ እና እሷ አንዳንዴ
ስትሄድ በመንገዷ ስሄድ በመንገዴ
ልትፈልገኝ ስትመጣ ልፈልጋት ስሄድ
ለፍለጋ እንወጣለን በሁለት ልዩ መንገድ
እሷም ልቤን ስታሳድድ እኔም ልቧን ሳሳድደው
እሷው ትመጣለች እኔው ለምሄደው
ጀርባዬን ስታየው ጀርባዬ ይያት እንጂ
አላያት አታየኝ
ላንገናኝ........
ፈላጊዬ ሆናለች ፈላጊዋ ስለሆንኩኝ
አንዳንዴ......
ለየቅል ጉዟችን ፍለጋ ስንማስል
ለሷ ይነጋና ለኔ ግን ይመሻል
ቀኑ ለሷ ሆኖ ሌቱ ለኔ ይሆናል
አንዳንዴያችን ቀጥሎ.....
ላሜ ልትሆነኝ ፍቅር ልታስልበኝ
ወደ እኔ ስትመጣ
እኔዋ ጥጃዋም ፍቅር ወተት ልፈልግ
ከቤቴ ስወጣ
ልትፈልገኝ ስትወጣ ልፈልጋት እንደሄድኩኝ
ቤቴ ትደርሳለች ቤቷ እንደደረስኩኝ
የኔ እና እሷ እንዳንዴ......
ስትሄድ በመንገዷ ስሄድ በመንገዴ
አልተገናኘንም አልታደልንም አንዴ
ግጥምጥሞሽ ወዶን ሰምሮም አንገናኝ
ልትፈልገኝ ስትመጣ ልፈልጋት ስለሄድኩኝ።

ቴዲ ጌትነት።
ከወደዱት ለወዳጅዎ ያጋሩት!
@bewketuseyoum19
@bewketuseyoum19